የአየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጠግነው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገለፀ

Date:

በኒጀር ዋና ከተማ በደረሰ ጥቃት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት የአስካይ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጠግነው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አየር መንገዱ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ÷ ባለፈው ሐሙስ ጥር 21 ቀን  2018 ዓ.ም ሌሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰ መዘገቡን አስታውሷል፡፡

ሁለቱ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን÷ አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡም የአየር መንገዱ መረጃ አመልክቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...