የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ አቀረቡ

Date:

በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግሥት ትብብር የተዘጋጀው ሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ላይ መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ለጉባዔው ተሳታፊዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አክለውም ለልማት የሚደረጉ ድጋፎች በመቀዛቀዛቸው ምክንያት አፍሪካ ጫና ውስጥ እንደምትገኝ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ፈተና እንደገጠማቸው የገለጹ ሲሆን፤ አህጉሪቱ በግብርና፣ የገጠር ልማት፣ መሠረተ ልማት እና ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ተገማች ፋይናንስ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል፡፡

“ከእኛ አውድ ጋር የሚስማሙ ከአየር ንብረት ጋር የተዛመኑ መሳሪያዎች፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ግብርና ያስፈልጉናል። ቴክኖሎጂዎች ተመጣጣኝ እና የጋራ ሊሆኑ እንጂ ሊደበቁ አይገባም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የምግብ ስርዓት ለማስተካከልና የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ጠንካራና ቁርጠኝነት የተሞላባቸው እርምጃዎች በመውሰድ በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ ስለመቻሉም ገልጸዋል፡፡

በዚህም የሀገሪቱ ያካሄደችው ሪፎርም በስርዓተ ምግብ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመጡ ያደረገ መሆኑን አመላክተዋል።

መንግሥት የምግብ ስርዓትን ለማጎልበት ከ700 በላይ የተግባር እርምጃዎችን በመውሰድ፤ በ7 ክላስተር ከፌዴራል እስከ ክልል ብሎም ተቋማትን ያሳተፉ ሥራዎች እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ የምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ከሀገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ስርዓቱ ጋር በማጣጣም በተከናወኑ ተግባራት የተመዘገቡ ለውጦችን ያብራሩም ሲሆን፤ የምግብ ስርዓቱ አካታችና ዘላቂ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በስንዴ ልማት ራስን ከመቻል አልፎ ለውጭ ገበያ እስከማቅረብ ድረስ ሰፊ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደምትገኝ አብራርተዋል።

በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ እየሆነ ያለውና የስርዓተ ምግብን መሻሻል ዓላማው ያደረገው የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በአረንጓዴ አሻራ ከ46 ቢልዮን በላይ ችግኞች በመትከል የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ስለመሆኑም አንስተዋል።

ቀጣይነት ያለው፣ አካታች እና የማይበገር የምግብ ስርዓት ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገው የመሪዎች ጉባኤው ከሐምሌ 20 እስከ 22 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዚህም ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን አስመልክቶ ያገኟቸውን ስኬቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባሉ።

በዚህም ጉባኤ ላይ ያልተገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቪድዮ ለጉባኤው መልዕክት አስተላልፈዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...