የኢራን ተደራዳሪዎች ኢስላማባድ ፓኪስታን ገቡ

Date:


የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሙሐመድ ጋሊባፍ ልዑካኑን እየመሩ ፓኪስታን መግባታቸውን የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የበረራ እንቀስቃሴዎችን የሚቆጣጠረውና የሚለየው ፍላይትራዳር24 የኢራን መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁለት አውሮፕላኖች IRAN04 እና IRAN05 በኢዝላማባድ አቅራቢያ ማራፋቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ፓኪስታን ይህን ድርድር ማሰናዳቷ በዲፕሎማሲው ረገድ ትልቅ ስም እንደሚሆንላትም እየተነገረ ነው።

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸሃባዝ ሽሪፍም “ኩራቱ ለፓኪስታን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሙስሊም አገራት ነው” በሚል ገልፀውታል።

የኢራን ተደራዳሪዎች የአገሪቱን ፍላጎት በትክክል የሚያስፈፅሙ ናቸው ተብሏል።

ተወካዮቹ በየራሳቸው የስራ መስክ ስመጥር በመሆናቸው የቴህራንን ጥቅሞች ዳር ያደርሳሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል።

ከፓኪስታን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የድርድሩ መሰረታዊ ነጥቦች በግልፅ ቢቀመጡም የሁለቱም አገራት ተሳታፊዎች ከየት ጉዳያቸውን እንደሚጀምሩ እስካሁን ግራ አጋቢ ሆኗል።

ከመጨረሻው የጀኔቫው ድርድር ወይስ በአዲስ መልክ ፤አሊያም ከሆርሙዝ ይከፈት እና የሁለት ሳምንታት ተኩስ አቁም ይረጋገጥ የታወቀ  ነገር የለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...