በካናዳ ከሚገኘው ፊውቸር ፊት ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር ስምምነት

Date:

 

ስምምነቱ የስራ ስልጠና፣ በካናዳ የትምህርት ዕድልን የሚ ያካትት ነው።  

ወጋገን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተቀማጭነቱን ካናዳ ካደረገው ፊውቸር ፊት ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር  የመግባቢያ  ስምምት ተፈራርሟል። 

በክህሎት ልማት ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ በሥራ ገበያ ልማት እና ተያያዥ ጉዳች ዙሪያ በጋራ መሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ነው የተካሄደው፡፡  

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የፊውቸር ፊት ኩባንያ ዳይሬክተር እና በካናዳ የቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ምክትል ፕሬዝዳንት አብይ ሬይሞንድ ፥ ስምምነቱ አቅምና ዕድል ከክህሎት ጋር በማጣመር በአለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ድልድይ መሆን የሚችል ነው  ሲሉ ገልጸዋል።  

ኢትዮጵያ የስራ አቅምና ፍላጎት መኖሩን አንስተው ፤ የሚያስፈልገውን አቅም በሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ደረጃ  ብቁ ወደ ሆነ ተወዳዳሪ የክህሎት ባለቤት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የስምምነቱ ዋና አላማ የቅም ግንባታ መሆኑን ጠቁመዋል።  

ይህ ስምምነት ፥ ወጣቶችን በተገቢው መንገድ አሰልጥኖ ለገበያ የማዘጋጀት፣ ተቋማትን የማብቃት እና ዝግጁ  አሰልጣኞችን በመፍጠር ሂደት ውስጥ ብቁ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት  ዕድል የሚፈጥር ነው ያሉት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል ናቸው። 

በካናዳ ካለ ተቋም ጋር የመጀመሪያው ነው ያሉ ሲሆን ፥ ዜጎችን በማታለል ገንዘብና ጊዜያቸውን እየሰረቁ ያሉ አካላት አሉ ብለዋል።  

በትናንትናዉ ዕለት የተደረገው ስምምነት ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየ  እንዲሁም የካናዳ መንግስት እውቅና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።   

ምዝገባው ሲጀመር በማስታወቂያ የሚገለፅ ሲሆን  መስፈርቱን የሚያሟሉ ዜጎች ብቻ መመዝገብ እንደሚችሉና ለስልጠናው ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...