የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ተሟላ ኦንላይን ግብይት መግባቱን አስታወቀ

Date:

ባለፈው በጀት ዓመት የቀጥታ የበይነ መረብ ግብይት ስርዓት በመተግበር ነጋዴዎች ባሉብት ሆነው እንዲገበያዩ ሲሠራ የቆየው ምርት ገበያው፤ በዘንድሮው ዓመት የኦንላይን ግብይትን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መርጊያ ባይሳ ተናግረዋል።

የግብይት ሥርዓቱ መተግበር ከጀመረበት ከሚያዚያ ወር ጀምሮ 12.5 ቢሊዮን ብር ዋጋ የሚተመን 127 ሺህ 830 ሜትሪክ ቶን ምርት ማገበያየት መቻሉን ጠቁመዋል።

የግብርና ምርቶች ግብይት ሥርዓትን በማዘመን፣ ግልፀኝነትንና መተማመንን በመፍጠር በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም አስረድተዋል።

የኦንላይን የግብይት ሥርዓቱ ምቹ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ፣ ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚያስችል ነው መባሉን ከስፑትኒክ ሰምተናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...