ትራምፕ ስለ ስደተኞች ምን አሉ?

Date:

የትራምፕ አስተዳደር የብኩርና ዜግነት መብትን ለማቋረጥ የያዙት እቅድ ላይ ውሳኔ  እንዲሰጥ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጠየቀ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ትላንት አርብ፥ የፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ  አስፈፃሚ የብኩርና ዜግነትን ማቆም ሕገ-መንግሥታዊ ነው ወይ በሚለው ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጠይቋል።

አስተዳደሩ በዚህ አመት ለሁለተኛ ጊዜ ነው ጉዳዩን ፍርድ ቤት እንዲያይለት ያቀረበው።

የብኩርና መብት (jus soli) የወላጆቻቸው ዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአሜሪካ ግዛት ውስጥ ለተወለዱ ሰዎች ዜግነት የሚሰጥ ህጋዊ መርህ ነው። 
ይህ አሰራር በሀገሪቱ ውስጥ በ14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሠረት የተጠበቀ ሲሆን፣ ይህም በአሜሪካ የተወለዱ ወይም ዜግነት የተሰጣቸው ሰዎች ሙሉ ዜጋ እንደሆኑ ይደነግጋል። 

ይሁንና ትራምፕ የስደተኞች ልጆች ሆነው በአሜሪካ የተወለዱ ህፃናት ዜግነት እንዳያገኙ የሚከለክለውን መመሪያም መፈረማቸው ይታወሳል፡፡ 

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዲ. ጆን ሳወር፥ ከአንድ
ምዕተ ዓመት በላይ ሲገዛ የቆየው የዜግነት መብት ለረጅም ጊዜ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም፥ በ14 ኛው ማሻሻያ ላይ የተሳሳተ አመለካከት እና አጥፊ ውጤት አለው ሲሉ ለፍርድ ቤት አስረድተው ፍርድ ቤቱ እንዲያጤነው ጠይቀዋል።

አዲሱ ይግባኝ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለአስተዳደሩ ወስኖበት ከነበረው የሚለየው፣ ክርክሩ አዘል እና የፌዴራል ዳኞች ቴክኒካዊ ጥያቄ በስፋት የታየበት መሆኑ እንጂ ፍሬ እንደቀደመው ፍሬ አልታየበትም። ዘገባው የሲኤንኤን ነው።
NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...