የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በይፋ ግብይት ጀመረ

Date:

ይፋዊ የግብይት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንክ ፕሬዚዳንቶችና የልማት አጋሮች በተገኙበት ተካሄደ።

ወጋገን እና ገዳ ባንኮች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሰነዶቻቸውን በማስመዝገብና ሌሎች መስፈርቶችን በማሟላት ግብይታቸውን በይፋ አስጀምረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግብይት መጀመሩ፥ የሪፎርም ስራዎችና የግሉ ዘርፍ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፥ መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል ጠንካራ የካፒታል ገበያ መመስረት አንዱ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን(ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ገበያው አስፈላጊ ዝግጅቶችና ሒደቶችን አልፎ በይፋ ግብይት መጀመሩን ገልጸዋል።

የግብይቱ መጀመር ለሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነም ተነግሯል።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች የገበያ መድረክ ሲሆን በመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት የተቋቋመ ነው።

የገበያው ዋና ዓላማ ውጤታማ የካፒታል ማሰባሰብ ስራዎችን በማጠናከር የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት እድገት ግልጽና ደህንነቱ በተጠበቀ የካፒታል ገበያ ስራዎች መደገፍ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...