ፈቃድ በሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብ መላክ ወንጀል ነው!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊ መንገድ የገንዘብ ማስተላለፍ ፈቃድ ያላቸውን 23 ድርጅቶች ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ፈቃድ በሌላቸው መንገዶች ገንዘብ መላክም ሆነ መቀበል በሕግ እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ፈቃድ ያላቸው ዋና ዋና ድርጅቶች ዝርዝር፦
✅ አቢሲኒያ ረሚት (Abyssinia Remit)
✅ አፍሪካ ኤክስቼንጅ (Africa Exchange)
✅ አላንሳሪ ኤክስቼንጅ (Alansari Exchange)
✅ አሪፍ ረሚት (Arif Remit)
✅ ብር-ሊንክ ረሚታንስ (Birr-Link Remittance)
✅ ቦሌ አትላንቲክ ኢንተርናሽናል (Bole Atlantic)
✅ ቦቲም መኒ ቴክኖሎጂ (Botim Money Technology)
✅ ካሽ ኤክስፕረስ (Cash Express)
✅ ደሃብሽል (Dahabshiil)
✅ ኢትዮ ሶሊሽንስ (Ethio Solutions) … እና ሌሎችም (በድምሩ 23 ድርጅቶች)።
ፈቃድ በሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብ መላክ በ “ሕገ-ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ” (Money Laundering) እንደመሳተፍ የሚቆጠር ከባድ ወንጀል ነው።
በሕገ-ወጥ ዝውውር ላይ የሚገኙ ገንዘቦች በመንግሥት የመወረስ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
ሕገ-ወጥ ዝውውር የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት በማዳከም የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ያደርጋል።
በውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችንም ሆናችሁ እዚህ ሀገር ውስጥ ገንዘብ የምትቀበሉ፣ ራሳችሁን ከሕግ ተጠያቂነት ለመጠበቅና ለሀገራችሁ ዕድገት የበኩላችሁን ለመወጣት ሁልጊዜም ሕጋዊ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ብቻ ተጠቀሙ።
