የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ 

Date:

በሦስት ተከታታይ መንግሥታት ሲታይ!

አይናለም እሸቴ 

ከባለፈዉ የቀጠለ – ከደርግ መውደቅ በኋላ በኢሕአዲግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ እግር ኳስ

    ግዮን መጽሔት :-ከደርግ ውድቀት በኋላ እግር ኳሳችን በአዲስ መንገድ እንዲዋቀር ቢደረግም በጊዜዉ የነበሩት የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ለኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታ እንዲዉል በመደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች እጥረት እየታየ መጥቷል፡፡ ሆኖም አንዳንድ በመሥሪያ ቤት የተመዘገቡ ለምሳሌ መድን፣ መብራት ኃይል የመሳሰሉት ቡድኖች የራሳቸው ሜዳ እንዲኖራቸውም ተደርጓል፡፡

   ከእዚህ ሌላ በአዲስ መልኩ በመቋቋሙ በክልል ደረጃ በጀት ተመድቦላቸው ትልቅ ደረጃ የደረሱ ቡድኖችም ተፈጥረዋል፡፡

ለምሳሌ

  • ድሬዳዋ ከነማ
  • ሀዋሳ ከነማ
  • ወላይታ ዲቻ
  • ፋሲል ከነማ
  • አርባ ምንጭ ከነማ 
  • አዳማ ከነማ ወዘተ… በዚህም ጊዜ ተጫዋቾች የተሻለ የደሞዝና የዝውውር ክፍያ ይከፈላቸው ስለነበረ ብዙ ተጫዋቾች ለማግኘት ትልቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በስተመጨረሻም ለክብር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ያለኝን ከፍተኛ አድናቆት ምስጋና ባቀርብ ደስ ይለኛል፡፡    

ስለ አቶ ይድነቃቸው ስም ሲነሳ በሄድኩባቸው አፍሪካ ሀገሮች ሁሉ የሚጠይቁኝ ይድነቃቸውን በቅርብ አይተኸው ታውቃለህ ወይ? የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው፡፡ አዎን ዘወትር ጨዋታ ሲኖር ስታዲየም ይገኛሉ ስላቸው በአግራሞት ታድላችኋል ይሉኛል፡፡ ይህ የሚያሳየው አቶ ይድነቃቸው ምንያህል የገዘፈ ዝናና ተወዳጅነት በአፍሪካ እንዳላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ኩራት ናቸው የምንለው፡፡ 

  አቶ ይድነቃቸውን ሳነሳ በጣም ወዳጄ የሆነውን አቶ ታደለ ይድነቃቸውን ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ከልጅነት ጀምሮ ወደ ስታዲየም ይዘውት ስለሚገቡ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ታሪክ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዋንጫና በኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ወድድሮች አቶ ይድነቃቸው ባላቸው የሥራ አስፈፃሚነት ዕድል ይዘውት ስለሚሄዱ እጅግ የጠለቀ ዕውቀት አካብቷል፡፡ ወደፊትም የተለያዩ መጽሐፍቶችን አዘጋጅቶ ያበረክታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 

  ታደለ ይድነቃቸው ሲነሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሥርዓተ ለውጡ ምክንያት ወደታች ወርዶ ስሙን ቀይሮ የቢራ ስም ተሰጥቶት ሊበተን በደረሰ ጊዜ ከሌሎች የቡድኑ ባለውለታዎች ጋር በመሆን በጀት ስላልነበረው ከኪሱ በማውጣት እንደገና እንዲያንሰራራ የገዘፈ ስሙን በማስመለስ በተከታታይ የኢትጵያ ዋንጫን እንዲነሳ በማድረግ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ እንደገና እንዲቋቋም እሸቱ ቀጭኑን ሰለሞን ሉቾን ማንሳት የግድ ይላል፡፡ እሸቱ ቀጭኑ በነ መንግሥቱ ዘመን በሁለት ቁጥር  ቦታ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ሲሆን ተጫዋቾች በመመልመልም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ ከአሠልጣኝ አሥራት ኃይሌ ጋር ምክትል አሰልጣኝ ኾኖም ሰርቷል፡፡ ሰለሞን ሉቾ በነበረው ችሎታ ብዙ ቡድኖች በከፍተኛ ገንዘብ ለመውሰድ ቢጠይቁትም ያሳደገኝ ቡድን ታች ወርዶ ወደ ላይ ሳላመጣው ለሌላ ቡድን አልጫወትም በማለት ያለውን የጠነከረ ፍቅር ያሳየ ለማልያው ታማኝ የሆነ ተጫዋችም ነው፤ ሰለሞን ሉቾ እንዳለውም ከአንድ አመት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞት ወደ ፕሪሚየም ሊግ ወጥቷል፡፡ በዚህ አቋሙ ሰለሞን ሉቸን ብዙ የስፖርት ቤተሰቦች ያደንቁታል፡፡

    ክብር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ አፓርታይድን መዋጋታቸውን ጨምሮ በጣም ታዋቂና ተወዳጅ ነበሩ፡፡ እኔ በተለያየ አጋጣሚ አፍሪካ አገሮችን ለማየት ዕድሉ ገጥሞኝ በሄድኩበት ደስ የሚለኝ ስለ እግር ኳስ መወያየት ነው፡፡ ታዲያ በአንድ ወቅት ኡጋንዳ ካምፓላ ከሀገሬው ሰዎች ጋር ስለእግር ኳስ አንስተው ስንወያይ አንዱ በእነ መንግሥቱ ጊዜ የነበረውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በማድነቅ እዚህ እየመጡ ያሸንፉን ነበር፤ በተለይ መንግሥቱ፣ ኢታሎንና ሉቻኖ ቫሳሎን ስማቸውን በመጥቀስ ስለ ችሎታቸው ሲመሰክሩ በተለይ መንግሥቱ ወርቁ ፍጥነቱ፣ የማታለል ችሎታው እንዲሁም ከሰዉ በላይ እየዘለለ በጭንቅላቱ ማስቆጠሩን በማድነቅ መስክረውልኛል፡፡   በመጨረሻም ለአንድ ሀገር እግር ኳስ እድገት በርከት ያለ ሜዳ በየአካባቢው ማዘጋጀት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ይህ ሊታሰብበት ይገባል፡፡

ያለበቂ ሜዳ እግር ኳስ ተጫዋች ማፍራት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ አሁን አንዳንድ ሜዳዎች ትንሽም ቢሆን በጥሩ ሥራ አምሮ በሽቦ ታጥሮ አይቻለሁ፡፡ ግን በአብዛኛው ተቆልፎበት ነዉ የማየዉ፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች እንደሚያወሩልኝ ለመጫወት በከፍተኛ የገንዘብ ክፍያ ነው ብለውኛል፡፡ አንዳንድ የቀድሞ ተጫዋቾች ታዳጊዎችን ሲያሰለጥኑ አይቻለሁ፣ ዉስጡን ባላውቅም አንዳንድ ወዳጆቼ እንደነገሩኝ ከፍ ያለ ክፍያ ይጠየቅበታል ብለዉኛል፡፡ ሆኖም ሁኔታዎች ቢስተካከሉ ገና ከልጅነታቸዉ የተለየ የኳስ ጥበብ የተካኑ ልጆችን ማግኘት ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ አሁን ያለው ፌዴሬሽን መልካም የሆነ ጅምር እንዳለው አይቻለሁ። በተለይም ለታዳጊዎች አሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት የኪስ ገንዘብን በማመቻቸት ታዳጊዎች እንዲወጡ የበኩሉን ጥረት እያደረገ መሆኑን ተገንዝብያለሁ። 

በዚህ ረገድ በአንድ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራን የማግኘት ዕድሉ ገጥሞኝ በወጣቶች ላይ ለምን አናተኩርም ብያቸው ፌዴሬሽናቸዉ የደረሰበትን የወጣቶች ስልጠናን አዳዲስ አሰራር በሚገባ ስለ አስረዱኝ አድናቆቴን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ቡድናችን ከ22 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ የዚሁ ፕሮጀክት ውጤት ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ እንደዚህ ዐይነቱ ጥረት የቀጠለ እንደሆነ ታዳጊዎቹ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮ የመቆየት እድሉ ስለሚገጥማቸው ለወደፊት ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለማግኘት የሚረዳ ይመስለኛል፡፡

    ጽሑፌን ሳጠቃልል ማንሳት የምፈልገው አሁን በመሠራት ላይ ያለው አደይ አበባ ዘመናዊ ስቴዲየም መቼ እንደሚያልቅ ባይታወቅም፣ ስሙን የአፍሪካ ጀግና ልጅ በሆኑት በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ስም እንዲሰየም ሐሳቤን እየወረወርኩ መላው የስፖርት አፍቃሪም ለዚህ ሐሳቤ ድጋፍን እንደሚሰጠኝ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ ለዛሬ አበቃሁ በሌላ ርዕሰ ጉዳይ ዳግም እንደምንገናኝ ዕምነቴ ነው፡፡

ከዝግጅት ክፍሉ:-

የዚህ ጥንታዊ ጽሑፍ አቅራቢ አቶ ዓይናለም እሸቴ ይባላሉ፡፡ አቶ አይናለም እሸቴ ተወልደው ያደጉት መርካቶ ቀድሞ ሰባተኛ በሚባል አካባቢ ሲሆን፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት እዚያው አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ ልዑል መኮንን /ቤት ነው፡፡ ልዑል መኮንን /ቤት በስፖርት እንቅስቃሴው በተለይም እግር ኳስን በጣም ያዘወትሩ ነበር ፤ አቶ ዓይናለምም ለእግር ኳስ ያላቸው ፍቅርን ቃላቶች የመግለፅ አቅም የላቸውም ፤ እግር ኳስን ከልባቸው የሚወዱት፡፡ አቶ አይናለም  በግዜው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በሁለተኛ ዲቪዥን ተመዝግቦ በሚጫወት ቡድን ውስጥ ተጫውተው አሳልፈዋል፡፡ 

በኋላም የመንግሥት ለውጥ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኞችና በቀበሌዎች ሲዋቀር አቶ ዓይናለም እሸቴ በመኖሪያቸው አካባቢ ከፍተኛ 6 ውስጥ በስፖርቱ አመራር ውስጥ በመሳተፍ በወቅቱ 25ቱም ከፍተኞች በተደረገው የእግር ኳስ የዋንጫ ውድድር ከፍተኛ 6 አሸናፊ ሆኖ ዋንጫውን ሲወስድ ከሌሎች የከፍተኛው አመራሮች ጋር በመሆን የእግር ኳሱን ቡድኑን በመምራት ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ ከፍተኛ 6 የሙዚቃ ቡድንም 25ቱም ከፍተኞች በተደረገ ውድድር ብሔራዊ ቲያትር በጥላሁን ገሠሠ ዳኝነት አሸናፊ ሆኖ ዋንጫውን ሲቀበል አቶ አይናለም እሸቴ ከፍተኛ ድጋፍ ነበራቸው፡፡ በዚህ ግዜ ትልቁ ድርሻ በወቅቱ የከፍተኛ ፀሐፊ እና በኋላም ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ተክሉ ካሳ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ 

አቶ ዓይናለም በተጨማሪም ለአትሌቲክስ ልዩ ፍቅር ስላላቸው ከወጣትነት ጀምሮ በጣም ይከታተሉ ነበር፡፡ በአበበ ቢቂላ የአትሌት ማሞ ወልዴ፣ የአትሌት ምሩፅ ይፍጠር፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌትጥሩነሽ ዲባባ፣ አትሌት መሠረት ደፋር አድናቂ ናቸው፡፡ በተለይም ለአትሌት ኃይለ /ሥላሴና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የተለየ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ አቶ አይናለም እሸቴ ለሙዚቃም ልዩ ፍቅር ስለነበራቸው በጊዜው ክቡር ዘበኛ፣ ፖሊስ ሰራዊት፣ ምድር ጦርና ለሎችም የሙዚቃ ባንዶች ዝግጅቶቻቸውን ሲያቀርቡ በየቦታው እየተገኙ ይታደሙ ነበር ፤ በዚህ ፍቅራቸው የተነሳ እነጥላሁን ገሰሰ፣ መሐሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ታምራት ሞላ፣ ሰይፉ ዮሐንስና ሙሉቀን መለሰ ጋር የቅርብ ጓደኝነት ነበራቸው፡፡ በተለይም ጥላሁን ገሰሰና ሙሉቀን መለሰ ጋር በጣም ይቀራረቡ ነበር፡፡ አሁን ካሉትም ከንዋይ ደበበና አረጋኸኝ ወራሽ ጋር የቅርብ ወዳጅነት አላቸው፡፡

አቶ አይናለም በወቅቱ ይሰሩበት በነበረው ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ፋብሪካ የንግድ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ለእግር ኳስ በነበራቸው ፍቅር በፋብሪካው የእግር ኳስ ቡድን በማቋቋም እሳቸው በመጫወት በፋብሪካው ኢንዱስትሪ ውስጥ ፋብሪካው ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን የጎላ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ 

አቶ አይናለም ባላቸው የተካበተ የስፖርት ታሪክ ለትውልድ እንዲያካፍሉ በተለያዩ የስፖርት ጋዜጠኞች ሲጠየቁ በደስታ ያላቸውን የታሪክ እውቀት ሳይሰስቱ በማካፈልም ይታወቃሉ፤ 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...