በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ገመዶች ላይ የሚሰቀሉ ባለቀለም ኳሶች ሚስጥር

Date:

በከተማችንም ሆነ በገጠር አካባቢዎች በሚገኙ የከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ አልፎ አልፎ የሚታዩት ባለቀለም ኳሶች ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆነው ይቆያሉ።

እነዚህ ኳሶች ለጌጥ ወይም ለኤሌክትሪክ ቁጥጥር የሚውሉ ሳይሆኑ እጅግ ወሳኝ የሆነ የደህንነት ተግባር አላቸው።

እነዚህ ኳሶች በቴክኒክ አጠራራቸው የአየር ላይ ምልክት ሰጪ ሉሎች (Aerial Marker Spheres) የሚባሉ ሲሆን ዋና አላማቸውም ዝቅ ብለው ለሚበሩ አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች የታይነት ምልክት መሆን ነው።

የኤሌክትሪክ ገመዶች ቀጭን በመሆናቸው አብራሪዎች ከአየር ላይ ሆነው በሩቅ ለማየት ስለሚቸገሩ እነዚህ ደማቅ ኳሶች ገመዶቹ ያሉበትን ከፍታ እና አቅጣጫ በግልጽ እንዲለዩ ይረዱታል።

ኳሶቹ አብዛኛውን ጊዜ ብርቱካናማ፣ ቀይ ወይም ነጭ ቀለማት የሚቀቡት ከአካባቢው ሰማይ ወይም ተፈጥሮ ጋር ተቃራኒ በመሆን በሩቅ እንዲታዩ ተብሎ ነው።

በተለይም በአየር ማረፊያዎች አቅራቢያ፣ በታላላቅ ወንዞች ማቋረጫዎች እና በሸለቆዎች ላይ በሚዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ እነዚህ ኳሶች የግድ መኖር አለባቸው።

ምንም እንኳን ኳሶቹ በኤሌክትሪክ ገመዶች ላይ ቢሰቀሉም በውስጣቸው ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ክፍል ወይም ሽቦ የላቸውም። ከፕላስቲክ ወይም ከአሉሚኒየም የሚሰሩ በመሆናቸው ቀላል እና ለረጅም ጊዜ ዝናብና ፀሐይን መቋቋም የሚችሉ ናቸው።

ይህም የአየር ትራንስፖርት ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን እና አውሮፕላኖች ከኤሌክትሪክ መስመሮች ጋር ተጋጭተው የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...