የኤን. ኤም ሲ ሪልስቴት 45 ቤቶች ምርቃት እና ቁልፍ እርክክብ አካሄደ

Date:

ነሐሴ17 2017 ዓ.ም  አለም ባንክ ቱሉ ዲምቱ በሚገኘው የኤን. ኤም ሲ የግንባታ ቦታ ላይ የተጠናቀቁትን 45 ቤቶች ምርቃት እና ቁልፍ እርክክብ ተካሂዷል ።

በሪልእስቴት  ልማት ላይ ከድርጅቱ ጋር አብረው ለስሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች የጋራ አልሚዎች የእውቅና ስርተፍኬት እና ዋንጫ ሽልማት ተሰጥቷል ፡፡

እንዲሁም በድርጅቱ ለሚደገፉ 200 ህጻናት እና 300 አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የአስቤዛ ድጋፍ ተደርጓል  ሌሎች መርሀ ግብሮችም ተካሄደዋል።

ኤን.ኤም ሲ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በንግድ ስሙ ኤን ኤም ሲ ሪል ስቴት በ2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወስኖ 35000 ካሬ መሬት ቦታ በሊዝ እንደተሰጠዉ ይተወቃል።

በተሰጠዉ ቦታ ላይ ከ1000 በላይ አፓርትመንት ቤቶችን ፣ሞሎችን እንዲሁም 63 ጂ+2 ቤቶችን ለመገንባት አስቦ 41 ጂ+2 ቤቶችን አውቀትናና ሀብት ካላቸው ግለሰቦች ጋር በጋራ አልምቷል።

በአዲሱ ሪል እስቴት አዋጁ መሰረት የግንባታዉን 80% በላይ ለአጠናቀቁና የሚጠበቀባቸውን ክፍያዎች በወቅቱ ለከፈሉ የጋራ አልሚዎች በነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል እና በነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በእስካይ ላይት ሆቴል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና ቁልፍ አስረክቧል።

ኤን ኤም ሲ ሪል እስቴት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የቤት ችግር ለማቃለል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በሚገመት ካፒታል የተጀመረው የድርጅቱ የግንባታ ስራ 576 አፖርትመንት ቤቶችን ሰርቶ የማጠናቀቅ እቅድ አለው፡፡

በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ኤን.ኤም ሲ ሪል ስቴት በአሁኑ ወቅት አህት ኩባንያ ከሆነው ቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጋር በመተባበር በሪል እስቴት በማኒፋክቸሪንግ ፣ በሆቴል፣ በትራንስፖርት፣ በቱርና ትራቭል ፣ በአስመጪና በላኪነት፣ በመኪና ኪራይ ተሰማርቶ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

የኤን ኤም ሲ ሪል እስቴት መስራች እና ባለቤት አቶ መሰረት መኮንን ሀገር ወዳድ እና የበጎ አድራጎት ስራ ቀንደኛ ተሳታፊ በመሆን ሙሉ ወጪያቸውን በመቻል የሚያሳድጓቸው 200 ወላጅ አልባ ህፃናት ያሉት ሲሆን በተጨማሪም ሁል ጊዜ በበዓላት ወቅት አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የአስቤዛ ድጋፍ ያደርጋል ።

ድርጅቱ በከተማው ለሚደረጉ የልማት ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረበለት ጥሪ መሠረት ለአቅመ ደካሞችና ለድሀ ድሀ ነዋሪዎች የሚያገለግሉ ቤቶችን ሠርቶ አስረክቧል ።

ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ጋር በመዋዋል በቀን 30 ሺ ዜጎች ዳቦ እንዳያገኙ አድርጓል ።

ከዚህም ባሻገር የሽገር ዳቦ ሱቆችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 13ቱም ወረዳዎች እንዲገነባ አድርጓል።

በተጨማሪም በአቃቂ ቃሊቲ ክፋለ ከተማ የሚገኘውን የቱሉ ዲምቱን አደባባይ 10 ሚሊዮን ብር በማውጣት የግንባታ እና የማስዋብ ስራ ሰርቷል፡፡

እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲን መሬት ኤጀንሲ ቢሮ ከ350 ሺህ ብር በላይ በማውጣት አስውቧል፡፡

ነሐሴ17 2017 ዓ.ም አለም ባንክ ቱሉ ዲምቱ በሚገኘው የኤን. ኤም ሲ የግንባታ ቦታ ላይ የተጠናቀቁትን 45 ቤቶች ምርቃት እና ቁልፍ እርክክብ ተካሂዷል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...