የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ እየተሰራ ነው

Date:

የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ያዘጋጀው 22ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል።

በ22ኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በቀጣይ ዓመት የሀገሪቱን የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ እየሰራን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ተግባራዊ በተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች እየታዩ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በማሻሻያው የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲጨምር የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው በዚህም አበረታች ለውጥ መኖሩን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት ያደረገው 22ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን አራዳ ሰምቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...