የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ጋር

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በስልክ መነጋገራቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ዛሬ ባደረጉት የስልክ ውይይትየመረጋጋት እና የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ እድገት እንዲሁም የአፍሪቃው ቀንድን በተመለከተ ሁለቱ ሃገራት በሚጋሯቸው ግቦች ላይ ማተኮራቸውን አመልክቷል።

በዚህ ውይይትም የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሪቢዮ ውይይት እና አካባቢያዊ መረጋጋት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት መስጠታቸውም ተጠቅሷል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ ባወጣው መረጃ ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያን የኤኮኖሚ ማሻሻያዎች ማድነቃቸውን በማመልከት፤ ለአሜሪካ የንግድ እና የመዋዕለንዋይ ፍሰት አማራጭ የመሆን አቅም ለመኖሩ አጽንኦት መስጠታቸውንም አክሎ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...