የግል ድርጅቶች ለጡረታና ለገቢ ግብር በሚል እየቆረጡ ቢሆንም ተገቢውን አይከፍሉም

Date:

በአዲስ አበባ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት የግል ድርጅቶች ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ ላይ ለጡረታና ለገቢ ግብር በሚል እየቆረጡ ቢሆንም፤ ተገቢውን ከፍያ ለመንግሥት ገቢ እንደማያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

በከተማዋ በሚገኙ አንዳንድ ተቋማት ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ መንግሥት በማያውቀው መልኩ እንደሚቆረጥባቸውና ጉዳዩም አሳሳቢ እንደሆነ በደረሰው ጥቆማ መሠረት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮን ስለጉዳዩ ጠይቋል፡፡

በዚህም የግል ድርጅቶች ከሠራተኞች ደመወዝ የገቢ ግብርና የጡረታ ክፍያ በትክክል የሚከፍሉ የግል ድርጅቶች ከ40 በመቶ እንደማይበልጡ እና ቀሪዎቹ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ መንግሥት በማያውቀው መንገድ ገንዘቡን እንደሚቆርጡ የቢሮው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሰውነት አየለ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል።

ኃላፊው በአዲስ አበባ ከተማ የደመወዝ ግብር በትክክል የማይከፍሉ የግል ተቋማት ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን ገልጸው፤ ቢሮው ችግሩን ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመሳሳይም በደረጃ ‘ሀ’ ግብር ከፋይ ሆነው በትክክል የማይከፍሉት ከ60 በመቶ በላይ ናቸው ሲሉ የተናገሩ ሲሆን፤ መሰል ቅሬታ እና ጥቆማም ቢሮ እንደሚደርሰው ኃላፊው ገልጸዋል።        

አክለውም በመሰል ሕገ-ወጥ ተግባራት ላይ እየተሳተፉ ያሉ ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ፤ ሙሉ ለሙሉ ችግሮችን ለመፍታትም ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት ትብብር ማድረግ እንሚገባው ገልጸዋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...