ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረችው እንደ ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ባሉ የማይበገሩ ጀግኖች መስዋዕትነት ነው።
የአየር ኃይላችን የ90 ዓመት ጉዞ ሲታሰብ፣ የነዚህ “የሰማይ ንስሮች” ታሪክ ምንጊዜም በደማቁ ይነሳል።
የጄኔራል ለገሰ አስደናቂ የጀግንነት ታሪክ፦
💥 የአየር ላይ ጀብዱ፦ በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ወቅት (1969-70 ዓ.ም) ‘F5-E’ የጦር ጄትን በማብረር፣ 2 የጠላት ‘ሚግ 21′ ጄቶችን አየር ላይ እርስ በርስ እንዲጋጩ በማድረግና ሌሎች በርካታ ጄቶችን በመጣል የማይረሳ ታሪክ ሠርተዋል።
📚 የታሪክ ምስክርነት፦ ኦስትሪያዊው የታሪክ አጥኚ ቶም ኩፐር ‘Wings over Ogaden’ በተሰኘ መጽሐፉ፤ የኢትዮጵያ አብራሪዎች በቁጥር ቢበለጡም በላቀ ክህሎታቸው ፍጹም የአየር ላይ የበላይነት እንደነበራቸው መስክሯል።
💪 ጽናትና መስዋዕትነት፦ በድሉ ዋዜማ በፊልቱ ግንባር ጄታቸው ተመትታ በፓራሹት ወርደው በጠላት እጅ ወደቁ። ይህን ተከትሎ ለ11 ዓመታት በሶማሊያ እስር ቤት አሰቃቂ ስቃይ ቢደርስባቸውም፤ ይህ ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር ሊያጠፋው አልቻለም።
🏅 የክብር ሽልማት፦ ከእስር ተመልሰው ሀገራቸው ሲገቡ በወቅቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የክብር ሽልማት የነበረውን “የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ወደር የለሽ ጀግና ሜዳይ” ተሸልመዋል።
ዛሬም የአየር ኃይላችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ታጥቆ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሲቆም፣ የእነዚህ ጀግኖች ታሪክ ለትውልዱ ትልቅ የሞራል ስንቅ ነው።
