የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

Date:

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ እና በጎንደር የእምነቱ ተከታዮችና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች በተገኙበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም በዝዋይ ሐይቅ ደሴቶችና በምንጃር ሸንኮራ ኢራምቡቲ በድምቀት እየተከበረ ሲሆን፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ነው በሀይማኖታዊ ስነስርዓት እየተከበረ የሚገኘው፡፡

ትናንት የጥምቀት ከተራ በዓል በመላ ሀገሪቱ የተከበረ ሲሆን፥ በዚህም ታቦታቱ ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደየማደሪያቸው ባህረ ጥምቀት ገብተዋል።

በዛሬው ዕለትም በባህረ ጥምቀት ስፍራ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...