የፍትሕ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያን ይፋ አደረገ

Date:

የፍትሕ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር ያዘጋጀውን የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያ ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያው ለቤተሰብ፣ሕጻናትና ተጋላጭ ወገኖች የሕግ ጥበቃን ለማረጋገጥና ማህበራዊ ፍትሕን ለማስፈን የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

ኢዜአ እንደዘገበው መምሪያው በቤተሰብ ጉዳዮች ዙሪያ የሚነሱ የሕግ ጉዳዮችን በማስረጃና በተግባር ላይ በተመሠረተ አሠራር በመምራት መፍትሔ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በፍርድ ቤቶች ከሚቀርቡ ጉዳዮች መካከል በአራተኛ ደረጃ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ናቸው።

ቤተሰብ የህብረተሰብ መሠረት በመሆኑ፣ መንግሥት የቤተሰብን ጥበቃ ለማጠናከር ትኩረት እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

መምሪያውም በቀለብ፣ በልጆች አስተዳደግና ጉብኝት፣ በንብረት አስተዳደር፣ በፍቺና በንብረት ክፍፍል እንዲሁም ከቤተሰብ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ የሕግ ጉዳዮች ላይ የሚመራና የሚዳስስ መሆኑን ተናግረዋል።

ለቤተሰብ፣ ሕጻናትና ተጋላጭ ወገኖች የሚደረገውን የሕግ ጥበቃ ለማረጋገጥና ማህበራዊ ፍትሕን ለማስፈንም መምሪያው ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ቤተሰብ ፍትሕ መምሪያው ከዳኞች፣ ከትምህርት ተቋማትና ከባለድርሻ አካላት በተውጣጡ ባለሙያዎች ኮሚቴ በማቋቋም የተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል።

የመምሪያው ዝግጅት ሂደትም በማስረጃና በተግባር ላይ የተመሠረተ አሠራርን በመከተል መዘጋጀቱን አስታውቀዋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...