የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ!

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% ሆኖ መወሰኑን የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ባደረጉት ስብሰባ ያጸደቋቸው የማለፊያ ነጥቦች ፡-
•  🔹 ለመደበኛ ተማሪዎች፡ 50%
•  🔹 ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፡ 45%
•  🔹 ለኦቲስቲክ፣ ዳውን ሲንድረምና ኢንተሌክቹዋል ዲሴቢሊቲ ላለባቸው ተማሪዎች፡ 40%

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እንደገለጹት፤ በ2018 ዓ.ም 84,257 ተማሪዎች በ199 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፣ የዘንድሮው ውጤት ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት የተሻለ እድገት አሳይቷል።

የቢሮው ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው፤ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ከመደበኛ ትምህርት ውጪ የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱንና በተለይም በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ላይ ልዩ ስትራቴጂ ተነድፎ መተግበሩ ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል።

ኃላፊው ውጤቱ በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ለደከሙ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...