በጆቢ አቪዬሽን የተሰሩ የኤሌክትሪክ የአየር ላይ ታክሲዎች፣ በዚህ አመት መጨረሻ በዱባይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የዱባይ መንገዶችና ትራንስፖርት ባለስልጣን ሊቀመንበር ማታር አል ቴየር ትላንት አርብ ተናግረዋል።
ጆቢ አቪዬሽን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራውን የአየር ላይ ታክሲ የመጀመሪያ የሙከራ በረራ፣ በሰኔ 2025 በኤሚሬትስ ሰማይ ላይ በስኬት ያከናወነ ሲሆን፤ ይህም ዱባይ አገልግሎቱን ወደ ነባሩ የትራንስፖርት ኔትዎርክ ለማስገባት ያደረገችው ጥረት ትልቅ ስኬት ነው ተብሏል፡፡
መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ባደረገው ኩባንያ የተሰራው የጆቢ የአየር ላይ ታክሲ፤ በሰአት 320 ኪሎ ሜትር ፍጥነት፣ እስከ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ሊጓዝ ይችላል፡፡
