የባህልና ጥበባት ሚዲያ ፎረም የሚዲያ ጉብኝት መርሐ ግብር ማስጀመሪያ በጎንደር ከተማ ተካሄደ

Date:

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተቋቋመው የባህልና ጥበባት የሚዲያ ፎረም የሚዲያ ቱር ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩን በማስመልከት በጎንደር ከተማ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።

ፎረሙ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር የተሳለጠ የመረጃ ቅብብሎሽና ፍሰት እንዲኖር የቅንጅት ሥርዓትን ለመዘርጋት ዓላማ ተደርጎ የተመሠረተ ለመሆኑ በመግለጫው ተገልጿል።

የባህልና ጥበባት ሚዲያ ፎረም የዘርፉን እምቅ አቅም ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ፣ የሚዲያውን አቅም ለዘርፉ እድገት ለመጠቀም፣ አጀንዳዎችን በቀላሉ ለመስጠት እና የመረጃ ፍሰቱን ለማሳለጥ እንዲሁም ዘርፉ የሚሰጠውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማጉላት አስፈላጊ እንደሆነም በመግለጫው ተካቷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኃይማኖት ዓለማየሁ በመግለጫው ወቅት እዳስታወቁት የባህልና ጥበባት እንዲሁም የስፖርት ሚዲያ ፎረም ተመስርቶ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰው።

የባህልና ጥበባት ሚዲያ ፎረም ከተመሰረተ በኋላ በርካታ ስራዎችን እንደሰራ ከዚህም ውስጥ በመስከረም ወር የተከበሩ የአደባባይ በዓላት ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን እንደሰጡ እና በዓላቱን የማስተዋወቅ ስራ እንደሰራ ገልፀዋል።

ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አጀንዳዎችን በመቀበል ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግም ሲሰራ እንደነበር ወ/ሮ ሀይማኖት አክለዋል።

ከሁሉም የሚዲያ ዘርፍ የተቋቋሙ የባህልና ጥበባት ሚዲያ ፎረም 50 አባላት እንዳሉትም በመግለጫው ተጠቁሟል።

የባህልና ጥበባት ሚዲያ ፎረም በጎንደር ከተማ በመገኘት የኪን ኢትዮጵያ የባህልና የኪነጥበብ ዝግጅት እንዲሁም የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች የተሳተፉበትን የህዝብ ለህዝብ መድረክ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ ችሏል።

በተጨማሪም የአፄ ፋሲል ቤተመንግስትን እና በከተማዋ የሚገኙ የልማትና ስራዎችም በመጎብኘት የተከናወኑ የልማት ስራዎች እና ሁነቶች ሽፋን ማግኘታቸውም በመግለጫው ተኳቷል።

ፎረሙ በጥር ወር በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ሁነት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃርም በትኩረት ለመስራት መዘጋጀቱም ተገልጿል።

ፎረሙ ሀገር በቀል እውቀቶች ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት በማጥበብ ለማህበረሰቡ ተደረሽ የሚያደርግ እንደሆነም የፎረሙ ም/ሰብሳቢ አቶ በፍቃዱ አባይ አንስተዋል።

መክፈቻውን ጎንደር ላይ ያደረገው የባህልና ጥበባት ሚዲያ ፎረም በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ሥራዎችን እንደሚሰራም ም/ሰብሳቢው አሳውቀዋል።

መግለጫውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የፎረሙ ሰብሳቢና ፀሀፊ በጋራ ስጥተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...