ዳሸን ባንክ 50  የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን  ለኤሌጋንስ ድርጅት ፋይናንስ በማድረግ አስረከቧል

Date:


ዳሸን ባንክ በ”ሸሪክ” ከወለድ ነፃ አገልግሎቱ አማካኝነት ለኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት የመጀመሪያውን ዙር 50 ዘመናዊ ቢ.ዋይ.ዲ. E2 (BYD E2) የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ፋይናንስ በማድረግ አስረክቧል ፡፡

ኤሌጋንስ ተሽከርካሪዎቹን በኢትዮጵያ ለሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያውላቸው ሲሆን፣ የዳሸን ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ በዘርፉ የስራ ዕድሎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ባንኩ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ባደረገው ጥረት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ “አስደናቂ” ዕድገት ማስመዝገቡን የዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ አማን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እና ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማፍራት ችሏል ብለዋል፡፡

ባንኩ ከተሰበሰበው ሀብት ውስጥ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ከወለድ ነፃ በሆነ የፋይናንስ ሥርዓት ማቅረቡንም ጠቅሰዋል።

​”ሸሪክ” አገልግሎት ስኬት በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝቷል የተባለ ሲሆን፣ ባንኩ እ.ኤ.አ. በ2023 በባህሬን በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ “በኢትዮጵያ ጠንካራው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሰጪ” ተብሎ መሸለሙን አቶ  አምዱ  አስታውሰዋል፡፡

​ ርክክብ የተደረገባቸው 50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የዳሸን ሸሪክ መለያ የተለጠፈባቸውና ባንኩን የሚያስተዋውቁ ሲሆን፣ የሜትር ታክሲ ተጠቃሚዎች የጉዞ ክፍያቸውን በዳሸን ሱፐር አፕ በኩል  መክፈል ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...