የኢትዮጵያ 10 ከፍተኛ ግብር ከፋይ ተቋማት

Date:

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለመንግሥት ከፍተኛ ግብር ከከፈሉ 10 ድርጅቶች መካከል 7ቱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መሆናቸው ተገለጸ።

ኢትዮ ቴሌኮም 65.84 ቢሊዮን ብር ግብር በመክፈል የዝርዝሩን አናት ሲይዝ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ36.87 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ30.87 ቢሊዮን ብር ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

የግል እና የውጭ ኢንቨስትመንት ተቋማትን በመወከል ሄኒከን ቢራ (26.1 ቢሊዮን ብር)፣ አዋሽ ባንክ (15.77 ቢሊዮን ብር) እና ቢጂአይ ኢትዮጵያ (12.59 ቢሊዮን ብር) ከፍተኛ ግብር ከፋይ ሆነው ተመዝግበዋል።

የ10ሩ ከፍተኛ ግብር ከፋይ ድርጅቶች ሙሉ ዝርዝር፡

ኢትዮ ቴሌኮም — 65.84 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ — 36.87 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ — 30.87 ቢሊዮን ብር

ሄኒከን ቢራ — 26.1 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ መርከብና ሎጅስቲክስ — 22.2 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል — 18.31 ቢሊዮን ብር

አዋሽ ባንክ — 15.77 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት — 13.58 ቢሊዮን ብር

ቢጂአይ ኢትዮጵያ — 12.59 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን — 12.33 ቢሊዮን ብር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...