የመንግስታቱ ድርጅት ዓለም አቀፍ ማሪታይም ድርጅት (IMO) በሆርሙዝ ሰርጥ ዳግም ችግር ተፈጥሯል ማለቱን ተከትሎ ነዳጅ ሳይቀር የዋጋ ጭማሬ አሳይቷል።
ሰርጡ ዙሪያ ላይ አንድ የጭነት መርከብ ጥቃት ደርሶባታል።
በዚህም ድርጅቱ ሆርሙዝ ላይ የቆሙ መርከቦችን የማስወጣት ዕቅዱን አቁሟል።
ብረንት ያልተጣራ ነዳጅ (ዓለም አቀፉ የገበያው መመዘኛ) ሐሙስ አዳሩን እስከ 4 በመቶ ጭማሬ እንዲያሳይም በር ከፍቷል።
ዓለም አቀፉ የማሪታይም ድርጅት ሰርጡ ላይ የተፈጠረው ስጋት መርከቦችን ለማስወጣት የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲገታ አስገድዶታል።
መርከቧ በኢራን ጦር እንደተመታች ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ለሲ ኤን ኤን ተናግረዋል።
ኢራን በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዳልሰጠችም ታውቋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይል (አይ አር ጂ ሲ) ባልተፈቀደ መስመር ለሚንቀሳቀሱ መርከቦች ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በሀኃላ የተፈፀመ ጥቃት ሆኖም ተመዝግቧል።
የአልጀዚራ
