ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ የሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ አምባሳደር ሆነች

Date:

ሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ በ1968 ዓመት በቻይና ውስጥ የተመሰረተ ሲሆን ከ 200 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ምርቶቹን የሚልክ የመኖሪያ ቤት እቃ አምራች ድርጅት ነው።

ኬ መቅድም ጄነራል አስመጪ እና ላኪ ድርጅት በኢትዮጵያ የሚዲያን ምርቶች ከ2018 ጀምሮ በብቸኛነት እያስመጣ እንደሚገኝ ተገልጿል። ከሚያስመጣቸው ምርቶች መካከል ፍሪጅ ፣የልብስ ማጠብያ ማሽን፣ የእቃ ማጠብያ፣ የአየር ማቀዝቀዣ እና ማሞቂያዎች፣ የተለያዩ መፍጫዎች ተጠቃሽ ናቸው።

በአዲስ አበባ ውስጥ ዋና ዋና በሚባሉ ቦታዎች ላይ ከ 11 በላይ ብራንድ ሾፖች ያሉት ሲሆን እንዲሁ ለረጅም ጊዜያት አብረውን ከሚሰሩ ኤጀንቶች ጋር በመሆን ምርቶችን ወደ ክልሎች እየላከ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ሚዲያ ኤሌክትሮኒክስ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ጋር የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎችን ለመወጣት እና ህዝቡ ጋር ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

ድርጅቱ አርቲስቷን የመረጠው የተማረች፣ ቤተሰቦቿን የምትረዳ ፣ማህበራዊ ግዴታዎቿን በተቻላት መጠን የምትወጣ ስራዋ ላይ ብቻ የምታተኩር በመሆኗ ነው ሲሉ ቤተልሔም ብዙአየሁ የድርጅቱ ማርኬቲንግ ኃላፊ ተናግረዋል።

ድምጻዊቷ ለአምባሳደርነት ምን ያህል ተከፈለሽ ተብሎ ለተነሳላት ጥያቄ የጠየኳቸውን በቂ ገንዘብ ከፍለውኛል ስትል ምላሽ ሰጥታለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...