ዶሮ አርቢዎች ስጋት ላይ መኾናቸው ተገለጸ

Date:

ዶሮ አርቢዎች በሚታየዉ ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ የመክሰር አዝማሚያ ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ያልተመጣጠነ የፍላጎት እና አቅርቦት የገበያ ሁኔታ ለአነስተኛ የዶሮ አርቢዎች ህልዉና ስጋት ሆኗል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀነባባሪዎች ማህበር መንግስት ምርታማነትን ብቻ አላማ ከማድረግ በበለጠ ገበያዉን ሊፈጥር ይገባዋል ሲል ጠይቋል።

የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዝናዉ ፀሀይነህ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ በአነስተኛ የዶሮ ማርባት ስራ ላይ ያሉ አርቢዎች ችግሩ ምርትን በብዛት ለመድፋት እና ለማስወገድ እንዲገደዱ አድርጓቸዋል ብለዋል።

ከፍተኛ የእርባታ ስራ ላይ ያሉትም ቢሆን በአንፃራዊነት ለመቋቋም ቢችሉም ዘርፉ ካለበት ችግር አኳያ ከስራ እንዳይወጡ መስጋት እንደሚያስፈልግ አቶ ዝናዉ ጸሀይነህ ገልፀዋል።

በተቃራኒዉ የምርት እጥረት ሲገጥም ደግሞ የሚኖረዉ የዋጋ ጭማሪ ማህበረሰብ እየተጎዳ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

ከ 160 በላይ በዶሮ እርባታ እና ማቀነባበሪያ ላይ የሚሰሩ አባላት አሉኝ የሚለዉ ማህበሩ በቅርቡ የዶሮ ገበያ ጥናት ለማድረግ እቅድ ስለመያዙ ሰምተናል።

የገበያ መጥፋት ሲገጥም ምርቱ እንዳይበላሽ ለማድረግ የሚያግዙ የመሰረተ ልማት በተለይም የኘሮሰሲንግ አሰራሮችን በመዘርጋት ምርቱን ከኪሳራ ማዳን ያስፈልጋል ተብሏል።

በተጨማሪም በከተማዉ ለታየዉ የእንቁላል ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የሆነዉን የዶሮ መኖ ዋጋ በዘርፉ ያሉ የግል ባለሀብቶችን በመደገፍ ማረጋጋት ያስፈልጋል ሲሉ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል።

መንግስት እንደ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጭማሪ ያሉ ዘርፉን እየጎዱት ላሉ ችግሮች ፈጣን ምላሽ እንዲሁም የገበያ አማራጮችን ማበጀት ካልቻለ አምራቹ ፍራቻ ዉስጥ ይገባል ሲል ማህበሩ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለ2018/19 በጀት አመት 22.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው

ከታቀደው 22 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ኩንታል እስካሁን  20...

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...