ከታቀደው 22 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ኩንታል እስካሁን 20 .9 ሚሊዬን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ መፈፀሙን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢንቨስትመንት እና ግብዓት ዘርፍ ማኒስትር ድኤታዋ ሶፊያ ካሳ መናገራቸውን ተመልክታለች ።
ሚኒስሩ ይህንን ያለው በዛሬው ዕለት በመጭው የመኸር ወቅት የግብርና ግብዓት አቅርቦትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።
ግዢ ከተፈፀመው የአፈር ማዳበሪያ መጠንም 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ በጅቡቲ ወደብ መድረሱን አስረድተዋል።
ጅቡቲ ከደረሠው የማዳበሪያ መጠን 12 ነጥብ 1 ሚሊዮን ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገልጿል ።
19.1 ሚሊዮን ኩንታል ለ2018/ 2019 በጀት አመት የቀረበ ማዳበሪያ መሆኑን የሚናገሩት ሚኒስትር ደኤታዋ ከቀረበው ማዳበሪያ ከህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 10.7 ሚሊዮን ኩንታል ለተጠቃሚዎች አሰራጭተናል ሲሉም ተደምጠዋል ።
ከዚሁ በተጨማሪ ሚኒስቴሩ በቂ መጠን ያለው የአፈር ማዳበሪያ ማከማቸቱን ጭምር አስረድተዋል ።
ከስርጭቱ ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተሠራጨው የማዳበሪያ መጠን 9 ነጥብ 66 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን ከዚህ አመት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት አለው ነው ያሉት ።
በተያዘው አመት መንግስት አርሶ እና አርብቶ አደሮችን እንዲሁም የሸማቹን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ ድጎማ ማድረጉን እና ይህም ድጎማ 84 ቢሊዮን ብር የማዳበሪያ ድጎማ ነው በማለት ድጎማው ወደ ኩንታል ሲቀየር 4972 ብር እንደሆነ ተናግረዋል።
ከምርጥ ዘር ጋር ተያይዞ 2 ሚሊዮን ኩንታል ለማቅረብ እንደታቀደ እና ወደ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ለተጠቃሚ ይሰራጫል ብለን እየሠራን ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
እስካሁንም ከ 6 ሚሊዮን በላይ የዘር ስርጭት መከናወኑን አሰረድተዋል ።
