የአሜሪካው ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ገዳይ ከሆኑ የኩላሊት በሽታ ዓይነቶች መካከል አንዱ የሆነውንና በኩላሊት ላይ ጠባሳን በመፍጠርና በመጨረሻም ኩላሊት ሥራውን እንዲያቆም በማድረግ እስከሞት የሚያደርሰውን በሕክምና አጠራሩ “ኔፍሮፓቲ” በመባል የሚታወቀውን የኩላሊት በሽታ ዓይነት ለማከም የሚያስችል “ቮይሳክት” የሚል መጠሪያ ላለው አዲስ መድኃኒት ማረጋገጫ መስጠቱን አስታውቋል።
“ኦሱካ” በሚባል መድሃኒት አምራች ኩባንያ የተመረተው ይህ መድሃኒት በሽታን ለመከላከል ከሚያስችሉ ነጭ የደም ሴሎች በቤተ ሙከራ የሚዘጋጅ ሲሆን ለሕመምተኛው በመርፌ መልክ የሚሰጥ ይሆናል።
መድኃኒቱ በየአራት ሳምንቱ የሚወሰድ ሲሆን በባለሙያ ወይንም ራሱ ታካሚው በቤቱ ሆኖ ሊወስደው በሚችል መንገድ መዘጋጀቱ መድኃኒቱን ይበልጥ ለአወሳሰድ ምቹ ያደርገዋል።
ኖቫሪቲሰ፣ ፋብሃልታ፣ ትራቬር ቴራፒቲክስ፣ ፊልስፓሪና ካሊዲታስ ቴራፒክስ ታርፒዮ በአሁኑ ሰዓት ይህንን የኩላሊት በሽታ ዓይነት ለማከም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ መድሃኒቶች ሲሆኑ በኦሱካ ኩባንያ የተመረተው አዲሱ “ቮይሳክት” መድሃኒትም በቅርቡ ገበያውን ተቀላቅሎ ጥቅም ላይ እንዲውል ከአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር ማረጋገጫን አግኝቷል።
የአዲሱ መድኃኒት ጥቅም ላይ መዋል በተለይም በአሁኑ ሰዓት ገዳይ ከሆኑ የኩላሊት በሽታ ዓይነቶች መካከል አንዱ የሆነውን የኩላሊት በሽታ ለማከም በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው “ቬራ ቴራፒቲክስ (VERA.O) ጋር በመሆን ገዳዩን የኩላሊት በሽታ በማከም ረገድ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው የኦሱካ ዋና ሜዲካል ኦፊሰር ጆን ክራውስ ለሮይተርስ መናገራቸውን ተመልክታለች።
አዲስ ማለዳ
