ግብፅ በሕዳሴው ግድብ ምክንያት ‘ለደረሰብኝ ጉዳት ካሳ ይከፈለኝ’ ስትል ጠየቀች

Date:

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል በግብፅና በሱዳን ላይ ላደረሰው “ጉዳት” የካሳ ክፍያ ሊፈጸም ይገባል ሲሉ የግብፅ የውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር በይፋ ጠየቀ።

ሚኒስትሩ ሃኒ ስዊለም፣ እሁድ ዕለት በግብፅ ሴኔት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፣ በዓባይ ወንዝ ላይ እንደ ሕዳሴው ግድብ ያለ ግዙፍ ግንባታ ያለ ጎረቤት ሀገራት ስምምነትና በአንድ ወገን ውሳኔ ተገንብቶ አያውቅም ብለዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ ግድቡ እስካሁን ባለው ሂደት ከግብፅ የ55 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ዓመታዊ የውሃ ድርሻ ላይ የ38 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ቅናሽ አስከትሏል። ይህ የውሃ መጠን መቀነስ በሀገሪቱ የውሃ ዋስትና ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ገልጸዋል።

የግብፅ ዓመታዊ የውሃ ፍላጎት 88.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የደረሰ ቢሆንም ሀገሪቱ የምታገኘው የተፈጥሮ ውሃ ግን 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ብቻ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ያለውን ክፍተት ለመሙላት ግብፅ 23.2 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ መልሳ ለመጠቀም እና 4.8 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በሕክምና ማጣሪያ ለማግኘት እየተገደደች እንደምትገኝ አስታዉቋል።

በግብፅ የአንድ ሰው ዓመታዊ የውሃ ድርሻ ወደ 500 ሜትር ኩብ ዝቅ ማለቱን የጠቀሱት ስዊለም፣ ይህም ከዓለም አቀፉ የውሃ ድህነት ወለል (1,000 ሜትር ኩብ) በግማሽ ያነሰ መሆኑንና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስረድተዋል።

በመስከረም በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረው የሕዳሴው ግድብ፣ 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በውስጡም 13 ተርባይኖችን ይዟል። ግድቡ በሱዳን ላይም ተጽዕኖ ማሳደሩን የጠቀሰው የሀገሪቱ ዘገባ፣ ባለፈው ጥቅምት 2025 የግድቡ የውሃ መለቀቂያ በሮች ሲከፈቱ በሱዳን የሮሴሬስ ወንዝ አካባቢ የጎርፍ መጥለቅለቅ ማስከተሉን እንደ ማሳያ አቅርቧል።

ይህ አዲስ የካሳ ጥያቄ የቀረበው፣ አሜሪካ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካኝነት በጉዳዩ ላይ ዳግም ጣልቃ ለመግባት ፍላጎት ባሳየችበት ወቅት ነዉ።

ኢትዮጵያ በበኩሏ ግድቡ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት እንደማያደርስና ፕሮጀክቱ ለቀጣናው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና ለጋራ ልማት ፋይዳው የላቀ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...