የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ለማክበር፥ አዲስ የሥነ ጽሑፍ ፌስቲቫል፥ የአአዩ ማሕበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ እና አአዩ ፕሬስ ባዘጋጁት ልዩ የመጻሕፍት ዓውደ ርእይ ላይ የ”ግጥም ንጋት” ተደግሷል።
ተወዳጁ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ጸሐፌ ወግ እና የጥበብ ሰው በእውቀቱ ስዩም፣ እንዲሁም በዕለቱ የተጋበዙ ገጣምያን ግጥሞቻቸውን ያቀርባሉ።
ኑ – ተመሰጡ – ተዝናኑ!!!
ቦታ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ዋናው ግቢ፣ ባህል ማእከል አጠገብ የመጽሐፍ ዐውደ ርዕይ ድንኳን ውስጥ
ቀን፡ አርብ፣ ታህሳስ 3
ሰዓት፡ ከጠዋቱ 4:00 – 6:00
