ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ለሚቀርቡ ናሙናዎች የፖሊዮ ምርመራ እንደምታደርግ ተገለጸ

Date:



ኢትዮጵያ ኤርትራን ጨምሮ ከሌሎች ጎረቤት አገራት የሚቀርቡ የፖሊዮ ቫይረስ ናሙናዎችን  ተቀብላ ምርመራ እንደምታደርግ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

በኢንስቲዩቱ የፖሊዮ እና መሰል በሽታ የተግባቦት አማካሪ አቶ ግርማ ሀይለማርያም ባለፉት ጊዜያት በሀገሪቱ ከተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ እንደ ሀገር የላብራቶሪ አቅምን የሚያሳድጉ ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ኢንስቲትዩቱ በፖሊዮ ቫይረስ የተጠቁት ዜጎችን ናሙና በመውሰድ የመመርመር ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የቫይረሱ አይነት ከየትኛው የፖሊዮ አይነት ጋር ሊገናኝ ይችላል የሚለውን ከሀገር ውስጥ ባለፈ ወደ ውጭ ተልኮ እንደሚመረመር እና እንደሚረጋገጥ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ሳይቀር የፖሊዮ ናሙና እንደምትቀበል የገለጹት አማካሪው፤ እንደ ማሳያም ኤርትሪያን ጠቅሰዋል፡፡

ባለፉት ጊዜያት ከተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እስከ አሁኑ የማል-በርግ ቫይረስ በሀገር ውስጥ ናሙና የመውሰድ እና ምርመራ የማድረግ ስራም እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት በሚቆይ የዘመቻ የፖሊዮ ክትባት በአገር አቀፍ ደረጃ 25 ሚሊየን የሚሆኑ ህጻናት እንደሚከተቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...