“ጦርነት መፍትሔ አይደለም”

Date:

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት በጽኑ በመቃወም፣ መንግሥታቸው ማንኛውንም ዓይነት የጦርነት አማራጭ እንደማይደግፍ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የስፔን ሕዝብ ይህንን ቀውስ እንደሚቃወም ገልጸው፣ እ.ኤ.አ. በ2003 የተካሄደው የኢራቅ ወረራ ዓለምን ይበልጥ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ማድረጉን እንደ ትልቅ ትምህርት አንስተዋል።

አሁንም በኢራን ላይ የሚደረገው ጥቃት ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓትን እንደማያመጣና ለሰው ልጅ ሕይወት መሻሻል ፋይዳ እንደሌለው አስገንዝበዋል።

ሳንቼዝ አሁን ያለውን ውጥረት “የሰው ልጅ ታላላቅ አደጋዎች መጀመሪያ” ሲሉ በመግለጽ፣ መንግሥታት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ዕጣ ፈንታ ላይ ቁማር መጫወት የለባቸውም ሲሉ አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...