የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እ.ኤ.አ. በ2022 በጥቁር ባህር የእህል ኢኒሼቲቭ ወደ ድሃ ሀገራት የተላከውን እህል በመመዝበር አውሮፓን ከሰዋል።በክሬምሊን ስብሰባ ላይ የሩሲያ የማዳበሪያ አምራቾች ማኅበር ኃላፊ አንድሬ ጉሪዬቭ እንደገለጹት “እህሉ ወደ ደቡብ የዓለም ሀገራት መሄድ ነበረበት” ብለዋል።
ጉሪዬቭ በተጨማሪም አውሮፓ የሩስያ ማዳበሪያን ከሶስት አመታት በላይ ለመጠቀም ሙሉ በሙሉ እምቢ ማለቷ የሰብል ምርትን በመቀነስ የማዳበሪያ ዋጋን ከ20 እስከ 30% ሊጨምር እንደሚችል የአሜሪካ ልምድ በማንሳት ተናግረዋል፡፡በዚህም ምክንያት የአውሮፓ ገበሬዎች መዝራትን መቀነስ ወይም ድጎማ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል፡፡
አውሮፓ በየዓመቱ 17 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያን ታስገባለች፤ ከዚህ ቀደም 5.5 ሚሊዮን ቶን ከሩሲያ አውሮፓ ስታስገባ ቆይታለች፡፡ እ.ኤ.አ. በ2022 የተጀመረው የጥቁር ባህር ኢኒሼቲቭ የዩክሬን እህል በጥቁር ባህር ወደቦች መላክ ብቻ ሳይሆን የሩሲያ የግብርና ምርቶችን እና ማዳበሪያዎችን ለአለም አቀፍ ገበያዎች መደበኛ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል ።
ይሁን እንጂ ምዕራባውያን ሀገራት እነዚህን ስምምነቶች ጥሰዋል፡፡ አብዛኛው የዩክሬን እህል ወደ አውሮፓ ይላካል፤ የሩሲያ ምርቶችን በተመለከተ ግን ግዴታዎች ሳይፈጸሙ ቀርተዋል፡፡በዚህ ምክንያት ሩሲያ በጁላይ 2023 ከስምምነቱ ለመውጣት መወሰኗ ይታወሳል።
