ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት በ “X” ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቡድን ከቀደመ ተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር፣ በህዝብ ኪሳራ የግልና የቡድን ጥቅሙን ለማስጠበቅ ስልጣንን የሙጥኝ ያለ ሃይል ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው አንጃው የህወሓት ቡድን (TPLF—D) በትግራይ ደቡባዊ ዞን ውስጥ አንዳች አይነት ተቀባይነት እንደሌለው የጠቀሱት ፕሮፌሰር ክንድያ ቡድኑ በዞኑ ህዝብ ያጣውን ህጋዊ ቅቡልነት (legitimacy) በሃይል ለማግኘት ከሰሞኑ የጀመረው እንቅስቃሴ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ካለችው እንስሳ ጋር የሚመሳሰል በቀቢጸ ተስፋ የገባበት የእውር ድንብር እርምጃ ነው ሲሉ ኮንነውታል።
