ለቱሪዝም ዘርፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለሙያዎች ሊሸለሙ ነው

Date:

ለቱሪዝም ዘርፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ ከ30 በላይ የሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎችን ሊሸልም እንደሆነ የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር አስታወቀ።

የእውቅና እና የሽልማት መርሃግብሩ ነሀሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም እንደሚከናወን ማህበሩ አስታውቋል።

ተቋሙ ሁለተኛ ዓመቱን በማስመልከት ይህንን ፕሮግራም ያዘጋጀ ሲሆን የሽልማት፣ የምስጋና እና የውይይት መድረኮች በመርሃግብሩ ተካታች እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

ተሸላሚ የሚደረጉት እጩዎች ከየተቋማቱ ተለይተው የሚላኩ እና በሕዝብ ከሚሰበሰብ ድምፅ አሸናፊዎች እንደሚለዩ ተነግሯል።

የህዝብ ድምጽ አሰጣጡ በአንላይን እንደሚድረግም ተገልጿል።

ሆቴሎች አስጎብኚዎች አሰልጣኞች ሼፎች እንዲሁም በአመራር ላይ ያሉ ሴቶች ዲያስፖራዎች እንዲሁም ሌሎች የቱሪዝም ዘርፉ ላይ የሚገኙ እና ቱሪዝምን የሚደግፉ አካላት ተሸላሚ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩ ከሽልማት እና ከምስጋና ባሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት መካከል ትብብርን ማጠናከር እና በዘርፉ ያለውን እድገት ለማሳየት አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።

(ሀገሬ ቴቪ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...