የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባለፈው የበጀት ዓመት ከአየር ጉዞ አገልግሎት 3.3 ቢሊየን ብር ማግኘቱን አስታወቀ
የአቪዬሽን ዘርፉን ለማሳደግ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የአየር ማረፊያዎችን እና አነስተኛ የሄሌኮፕተር ማረፊያዎችን እየገነባሁ ነው ብሏል።
ኢትዮጵያ በአሁኑሰዓት ፣ 20 የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዳሏትና 4 ተጨማሪ አውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታ ላይ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።
