ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ 731 ዜጎች በዘላቂነት ከቦታቸው እንዲነሱ ተደረገ

Date:

በአዲስ አበባ 247 ቦታዎች ለጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች የተጋለጡ ናቸው

በ64 ቦታዎች የጎርፍ መከላካያ ግንብ ተሰርቷል

በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ 247 ቦታዎች መለየታቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።

በከተማዋ የተሰራውን የጎርፍ መከላከል ስራ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ሰሞኑን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመው መጠነኛ ጎርፍ ከሚቲዎሮሎጂ ትንብያ አንጻር የሚጠበቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ ግዮን አካባቢ የተከሰተው ለጎርፍ መከላከል የተሰራውን ድጋፍ ጥሶ ወጥቶ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማዋ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው። ለጎርፍና ተያያዥ አደጋ ተጋለጭ የሆኑ 247 ቦታዎች ተለይተዋል።

በተለዩት ቦታዎች የጎርፍ ተጋላጭነትን ማቅለል መቻሉን አስገንዝበዋል።

በክረምቱ የጎርፍን ተጋላጭነት ለመቀነስ ግብረኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ አደጋ እንዳይከሰት አስቀድሞ የመከላከል እና አደጋ ከተከሰተ ፈጥኖ ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በወንዝ ዳር ፕሮጀክት የለሙትን ሳይጨምር 64 ቦታዎች የጎርፍ መከላካያ ግንቦች መሰራታቸውንም አስታውቀዋል።

ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችንም በጊዜያዊነት የማንሳት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በቤተል አካባቢ የተከሰተውም ለውሃ መፍሰሻ የተሰሩት መሰረተ ልማቶች በበረዱ በመዘጋታቸው መሆኑን ገልጸው፤ በረዶውን በማጽዳት ፈጣን ምላሽ ተሰጥቷል ብለዋል።

በተከሰተው ጉዳትም በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰና በንብረት ላይም የደረሰው ጉዳት መጠነኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

አጠቃላይ ጎርፉ ባስከተለው የጉዳት መጠን ላይ ዳሰሳ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል።

አንድ ጊዜ ጎርፍ በተከሰተበት ቦታ ላይ ድጋሚ እንዳይከሰት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በአጠቃላይ ጎርፍን መከላከል ላይ በተሰራው ስራ ተጋላጭነቱ መቀነሱን ተናግረዋል።

ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ 731 ዜጎች በዘላቂነት ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርጓል።

ለአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ኮማንድ ፖስት ተዘጋጅቷል።

በየሳምንቱ የክፍለከተማ አመራሮች የተካተቱበት ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው በተባሉ ቦታዎች ክትትል ይደረጋል።

ከሰሞኑ አነስተኛ የጎርፍ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጥናት እየተደረገ ይገኛል ያሉት ስራ አስኪያጁ የሁሉም ጥረት ይፈልጋል ብለዋል።

ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍል ሁሌም ተባባሪ እንዲሆን ተጠይቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...