”ለጦርነት ተዘጋጁ” አሜሪካ

Date:


 
የአሜሪካ የጦር ሚኒስቴር ዋሽንግተን ለጦርነት  መዘጋጀት እንዳለባት አሳሰበ።

የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር  ፔት ሀግሰት ለከፍተኛ የጦር ሀላፊዎች እና አዛዦች መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ዋሽንግተን በአስቸኳይ በጦርነት መንፈስ ውስጥ መግባት እንዳለባት ያስገነዘቡት ሀግሰት አገራቸውን ምን ስጋት እንዳለባት ግን ይፋ አላደረጉም።

ፔንታጎን በቅርቡ  ሁለት ወሳኝ የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጉንም ዘገባው አስታውሷል።

የብሄራዊ መከላከያ ስልቱን ከቻይና ወደ የውስጥ ደህንነት እና  ምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ማዞር አንደኛው ውጥኑ ሆኗል የአሜሪካ ጦር።

“ሰላምን ለማረጋገጥ ለጦርነት መዘጋጀት ይጠበቅብናል ” ብለዋል ፔት ሀግሰት።

በመቶዎች ለሚቆጠሩ የጦር አዛዦች በቨርጂኒያ የተናገሩት መከላከያ ሚኒስትሩ ውጥረት አሜሪካ እንዳለባትም አስጠንቅቀዋል።

ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካውን መከላከያ ሚኒስቴር ወደ ጦር ሚኒስቴር መለወጣቸው የዚህ  ዓይነቱ ዝግጅት እንዳለ አመላካች ነው።

ዋይትሐውስ ለ2026 የመከላከያ በጀት 1.01 ትሪሊዮን ዶላር እንዲሆን መጠየቁም ይታወሳል።

ቀደም ሲል ከነበረው በጀት የ13.4 በመቶ ብልጫ  ይኖረዋልም። ዘገባው የአር ቲ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...