ሌ/ጄነራል ታደሰ አዲስ አበባ ገቡ !

Date:

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ይሆን?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ በክልሉ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ዛሬ እሁድ መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጄነራሉ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ከከፍተኛ የፌደራል ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ የተገለጸ ሲሆን፣ ጉብኝቱ በትግራይ ክልል ባለው የጸጥታና የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል።

ይህ ጉዞ ትልቅ ትኩረት የሳበው ጄነራል ታደሰ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ተሰጥቷቸው የነበረው የአንድ ዓመት የሥልጣን ጊዜ ከሦስት ቀናት በኋላ (መጋቢት 30) ስለሚያበቃ ነው።

ጄነራሉ ለተጨማሪ ስድስት ወራት በሥልጣን ላይ ይቆያሉ ወይስ አዲስ ምትክ ይመደባል የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል። የአዲስ አበባው ውይይትም የጊዜያዊ አስተዳደሩን ቀጣይ እጣ ፈንታና የክልሉን የሽግግር ሂደት የሚወስን ወሳኝ ክስተት እንደሚሆን ይጠበቃል።

አውራምባ ታይምስ –

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...