ሕወሃት የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል ሲል ከሰሰ

Date:

ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ ሐሙስ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 ዓ፣ም ሌሊት በትግራይ ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል ሲል ከሠሠ።

የድሮን ጥቃቱ በትግራይ ጸጥታ ኃይሎች እና በነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ያለው ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በዚህ ጥቃት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ጥሷል በማለት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል።

የሕወሃት መግለጫ፣ የትግራይ ሕዝብ እና ሕወሃት ዳግም የሚቀሰቀስ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያደርስ በመግለጽ፣ የፌደራል መንግሥቱ ባለስልጣናት የግጭት ማቆም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ የሰላም መንገድን እንዲከተሉ ሲጠይቁ ቆይተዋል ብሏል።

የአፋር ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣናት ላለፉ ጥፋቶቻቸው በመጸጸት ፋንታ ፌደራል መንግሥቱ ላደራጀው ጸረ-ትግራይ ታጣቂ ቡድን ነጻ መሬት በመፍቀድ፣ የሌላ ዙር ጦርነት ማስፈጸሚያ መሳሪያ እየሆኑ ይገኛሉ የሚል ክስም ሕወሃት አቅርቧል።

የፌደራል መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም [ዋዜማ]

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...