በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም አንድ ሚሊዮን ብር ተቀጣ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር፣ በካይ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በመልቀቁ ምክንያት በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም (AHRI) ላይ አንድ ሚሊዮን ብር መቅጣቱን አስታውቋል። ይህ እርምጃ የተወሰደው፣ ከተመሳሳይ ወንዝ መበከል ጋር በተያያዘ ከሁለት ቀናት በፊት አለርት ሆስፒታል ተመሳሳይ ቅጣት ከተጣለበት በኋላ ነው።

ባለስልጣኑ ዛሬ እንዳስታወቀዉ፤ አርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም (AHRI) በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ ዘነበ ወርቅ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመሩን ከወንዝ ጋር በማገናኘት ብክለት ፈጽሟል።

በ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የመንግስት የጤና ተቋም የሆነው አለርት ሆስፒታል ደግሞ በተመሳሳይ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ውስጥ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ በካይ ቆሻሻ በመልቀቁ ምክንያት አንድ ሚሊዮን ብር ቅጣት ተጥሎበት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደበት ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች ቢሰሩም ከህገ-ወጥ ተግባራት የማይታቀቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...