ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ፣ “መንግሥት ምርጫውን ለማከናወን በቂ አቅም እና ዝግጁነት አለው” ብለዋል።
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እስካሁን በኢትዮጵያ ከተካሄዱ ምርጫዎች የተሻለ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም ሲሉም ገልጸዋል።
ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እና ብዘኃ ድምፆች ያሉት እንዲሆን መንግሥት በኃላፊነት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፣ “እኛ እንደ ፓርቲም፤ እንደ መንግሥትም ዝግጁ ነን፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከወዲሁ መዘጋጀት አለባቸው” ብለዋል።
