” መንግስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የመዝጋትም ሆነ የማዳከም ፍላጎት የለንም

Date:

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዋናዮች በዳግመ ምዝገባው ዙርያ ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ፣ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ መንግስት ተቋማቱን የማጥፋት እቅድ አለው እየተባለ ለሚቀርበው ቅሬታ በሰጡት አስተያየት፣ ” ይሔ አስተያየት ስህተት ነው፣ እነዚህን ተቋማት የማዳከም አላማ የለም ” ብለዋል፡፡

” ይልቁንም መንግስት እነዚህን ተቋማት የማጠናከር አላማና ፍላጎት ነው ያለው፣ የዳግመ ምዝገባና ምዘና ሒደቱ ትኩረትም ይህን እውን ማድረግ ነው ” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የዳግመ ምዝገባና ምልከታ ሒደቱ በአዲስ አበባ መጠናቀቁን ተናግረው፣ በቀጣይ የትኞቹ ተቋማት ይቀጥላሉ፣ የትኞቹ አይቀጥሉም የሚለውን ለመግለፅ ሪፖርት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባው የዳግመ ምዝገባና ምዘና ስራ በመጠናቀቁ፣ በቅርቡ በክልሎች ይህንን ስራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን አሉ ?

” አሁን እየተከናወነ ባለው ዳግመ ምዝገባና ምዘነና ሒደት የተፈለገው፣ የትምህርት ተቋማቱ መሰረታዊ በሆነ መንገድ ራሳቸውን እንዲያድሱ ነው፡፡

ባለቤትነታቸው እንኳ የማይታወቅና አጠራጣሪ የሆኑ ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች የማጥራት ስራ ነው እየተሰራ ያነው፡፡መዝጋት የምትፈልገውን ተቋም ይህን ያህል ጊዜ ማቆየት አያስፈልግም፡፡ በፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጠህ ከገበያ እንዲወጡ ማድረግ ይቻላል፡፡ ግን እሱ አይደለም አላማችን፡፡

የእኛ አላማ፣ ትናንሽ ቢዝነሶች ሆነው የጀመሩት ተቋማት ወደ አንድ ተደራጅተውና ተጠናክረው እንዲመጡ ነው፡፡ ካልቻሉ ደግሞ ከገበያው መውጣት አለባቸው፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ (ፕሮፌሰር ብረሀኑ ነጋ) ከዚህ በፊት የተናገሩት ነገርም (50 ተቋማት ይበቃሉ ማለታቸው ይታወሳል) ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ጠንከር ጠንከር ያላችሁ ተቋማት ሁኑ፡፡ ጥቂት ተቋማት ይበቃሉ፡፡ ይህ ሁሉ ተቋም አለ ማለት፣ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ነው ያሉት፡፡ ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ ተቋም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ የእኛም አላማ ይኸው ነው፡፡

ከዚህ በፊት ወጣ የተባለው፣ ‘ አብዛኞቹ ተቋማት መስፈርቱን አያሟሉም ተብለዋል ‘ የተባለው ዘገባ ስህተት ነው፡፡ ሚድያዎችን ለመተባበር ብለን የሰጠናቸውን መረጃ አዛብተው ዘገቡት፡፡ ከዛም፣ ሁሉም የግል ትምህርት ተቋማት መስፈርቱን አያሟሉም ተባለ ተብሎ ተስተጋባ፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡

በወቅቱ ያልነው፣ አብዛኞቹ ተቋማት ለዳግመ ምዝገባ የሚሆን የተሟላ ሰነድ አላቀረቡም ነው፡፡ ሰነድ አስገቡ ስንላቻው ስለነበር ማለት ነው፡፡ ሰነድ አላሟሉም ማለትና ያስገቡትን ሰነድ ገምግሞ መስፈርቱን አላሟሉም ማለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡

ቀደም ሲል ሒደቱ በጣም ቀላል ነበር ኮሌጅ ለመክፈት፣ ትንሽ ገንዘብ ካለህ አንድ ሁለት ክፍል ተከራይተህ መክፈት ነበር፡፡ በዚህ መሰሉ ሒደት መቀጠል አይቻልም አሁን፡፡ ይህን ቀላል አካሔድ የለመዱ ተቋማት መቀጠል አይችሉም፡፡ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው በትንሹ ኮሌጅ የሚያስብል ስራ ሰርተው ነው ይህንን ቢዝነስ መጀመርና ማስኬድ ያለባቸው፡፡

አሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በተቀመጠው መስፈርት መሰረት እንደ ኮሌጅ መቀጠል እችላለሁ የሚሉት ተቋማት ናቸው የተመዘገቡት፡፡ ከተመዘገቡት መካከል ደግሞ፣ አሁን ግምገማ ተደርጎ፣ ሰነዶቻቸው ተፈትሸው፣ የመስክ ምልከታም ተደርጎ፣ በትክክል መስፈርቱን ያሟላሉ የሚባሉትን ውጤት እንገልፃለን፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የአዲስ አበባን ተቋማት ምዝገባና ምልከታ ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል፡፡ ውጤቱን ለመግለፅ ሪፖርቱን በማዘጋጀት ላይ ነው ያለነው፡፡ ጎን ለጎን ደግሞ በክልሎች ይህንን ስራ ለመጀመር ቅድመ ዘግጅት እያደረግን ነው፡፡ ስራው በአዲሱ የበጀት አመት የሚጀመር ይሆናል፡፡

እስካሁን ከዘርፉ የወጡ ተቋማትን በተመለከተ የተለያየ አሀዝ ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ መጀመሪያ ላይ 84 ተቋማት ሳይመዘገቡ ቀሩ፡፡ በኋላ ላይ ግን ዘግይተው የመጡ አሉ፡፡ ከነሱ ውስጥ በቂ ምክንያት ያቀረቡትን መዝግበን እየገመገምን ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ተመዝግበው ከነበሩት ውስጥ ለመውጣት ሒደት ላይ ያሉ አሉ፣ ጎንለጎን ማለት ነው፡፡ ይህ የእነሱ ገባ ወጣ ማለት፣ ከዘርፉ የወጡ ተቋማት ብዛት በየጊዜው እንዲለያይ አድርጎታል፡፡ እንደዛም ሆኖ፣ አሁን የምዝገባና የግምገማ ሒደት ላይ ስለሆንን ትክክለኛ ቁጥሩን ማስቀመጥ ቢያስቸግርም ቢያንስ 80 የግል ትምህርት ተቋማት፣ ስራቸውን አቋርጠው ከዘርፉ ተሰናብተዋል፡፡

የዳግመ ምዝገባው መመሪያ ላይ በቂ ውይይት አልተደረገበትም፣ ከዘርፉ ተዋናዮች ግብአት አልተወሰደም የሚለውም ጉዳይ ትክክል አይደለም፡፡ ከተቋማቱ ባለቤቶች በሁለት መንገድ ግብአት ተቀብለናል፡፡ አንደኛው፣ ከውይይት መድረክ የተገኘው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በፅሑፍ የተቀበልነው ነው፡፡ በዚህ መንገድ በአዲስ አበባ በሀይሌ ግራንድ ሆቴል ከተደረገ ውይይትና በፅሑፍ ከቀረቡልን ሀሳቦች ግብአት ወስደናል፡፡አስፈላጊ የሆኑትንና ያስኬዳሉ የምንላቸውን ሀሳቦች በግብአትነት ተጠቅመንባቸዋል፡፡

ለምሳሌ ፦ ከእነሱ ተቀብለን ካካተትናቸው ሀሳቦች አንዱ፣ በመውጫ ፈተና ቢያንስ 25 በመቶ ያላሳለፈ ተቋም መቀጠል የለበትም የሚለው መስፈርት መቼ ተግባራዊ መሆን ይጀምር የሚለው ላይ የእነሱን ሀሳብ ተቀብለን የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጥ አድርገናል፡፡

ይህ መስፈርት መተግበር የሚጀምረው፣ መመሪያው በወጣበት ጊዜ ትምህርት በጀመሩ ተማሪዎች ላይ እንጂ፣ በነባር ተማሪዎች ላይ መሆን የለበትም የሚለው ሀሳብ ከነሱ የመጣ ነው፡፡ ይህ ሀሳባቸው አሳማኝ በመሆኑ ተቀበልነው፡፡ አሁን ለትግበራው ሁለት አመት ገደማ አላቸው፡፡ በ 2019 ዓ.ም ገደማ ነው መተግበር የሚጀምረው ይህ መመሪያ፡፡ ሌሎችም የተቀበልናቸው ሀሳቦች አሉ፡ ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

” መንግስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የመዝጋትም ሆነ የማዳከም ፍላጎት የለውም ” – የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...