በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ ጎዞ ሻሾ ቀበሌ ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ የግለሰብ መኖሪያ ቤት በሌሊት ሰብሮ በመግባት በሬዉን ከታሰረበት ፈቶ በመውሰድና ጫካ ዉስጥ ማሰሩን የዞኑ ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስም ሚያዚያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በታርጫ ዙሪያ ወረዳ ኮይሻ ቀበሌ በሬዉን ከታሰረበት በመፍታት እየጎተተ ሲወስድ ፍለጋ ከወጡ የመንደሩ ነዋሪዎች ጋር ፊት ለፊት መገናኘቱን በማሳወቃቸው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል።
በዞኑ በዓል ወቅት ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል የእርድ እንስሳት በመሆኑ ህብረተሰብ ሊጠነቀቅ ይገባል ተብሏል።
