መገናኛ ብዙኃን በነፃነት እንዲሰሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

Date:

የፕሬስ ነፃነት ቀን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አማካይነት በየዓመቱ ሚያዝያ 25 ወይም ሜይ 3 በመላው ዓለም ይታሰባል፡፡

በያዝነው ዓመትም “የፕሬስ ነጻነት ቀንን ስናከብር ዜጎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መረጃ እንዳይጭበረበሩ ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት እሳቤ የሚያጎላበት ቀን ሊሆን ይገባል፡፡” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ታስቦ ውሏል፡፡

አሐዱም ታስቦ የዋለውን የፕሬስ ነፃነት ቀን አስመልክቶ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እና የመብት ተሟጋቾችን ጠይቋል።

ለአሐዱ ሀሳባቸውን የሰጡት ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዳዊት አስታጥቄ፤ “ሚዲያው በነፃነት እንዲሰራ መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል” ብለዋል።

አክለውም “በኢትዮጵያ ያለው የሚዲያ ነፃነት ብዙ መሻሻሎች ሊደረጉበት ይገባል” ያሉ ሲሆን፤ በተለይም ጋዜጠኞች ሥራቸውን በነፃነት መስራት የሚችሉበት ሥነ-ምህዳር መፍጠር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀውን የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ በተመለከተ ሀሳባቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቿች ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ኃይለማርም በበኩላቸው፤ “አዲሱ አዋጅ ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ ታሳቢ በማድረግ ሊስተካከሉ የሚገባቸው አንቀጾች አሉት” ብለዋል።

በድሬድዋ ብዙኃን መገናኛ ቋንቋ ክፍል ላይ እያገለገሉ የሚገኙት አንዋር መሐመድ ደግሞ፤ “ያለ ፕሬስ ነፃነት ዴሞክራሲን ማረጋገጥ አይቻልም” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም መንግሥት በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጠውን የፕሬስ ነፃነት እንዲያከብርና ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል። 

“ሚዲያው ብዙ ፈተናዎችን እያለፈ ይገኛል” ያሉት አቶ አንዋር፤ “መንግሥትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻዎችና ኃላፊነት ካለባቸው አካላት ድጋፍ  ሊደረግለት ይገባል” ብለዋል። 

“ሚድያው ከለላ ያስፈልገዋል። ጋዜጠኞች ከስጋት ነጻ ሆነው መስራት አለባቸው” ያሉት ደግሞ ጋዜጠኛ አብርሃም ፀሀዬ ናቸው።

የመገናኛ ብዙኃን አሰልጣኝ የሆኑት አቶ አብርሃም፤ ጋዜጠኞች ከስጋትና ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ነፃ ሆነው የሚሰሩበት ምህዳር እንዲኖር ይጠበቃል ያሉ ሲሆን፤ ሙያተኞቹም ሕግ እና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ የሙያውንም ሥነ-ምግባር ጠብቀው መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።

የፕሬስ ነፃነት ቀን ሲከበር ቀኑን ከማክበር በዘለለ፤ መገናኛ ብዙኃን በቂ የሆነ ነፃነት መጎናፀፍ እንዳለባቸው አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...