አዲስ ቻምበር ከ482 ሺህ በላይ ነጋዴዎችን አባል ለማድረግ በክፍለ ከተማ ደረጃ አደረጃጀቱን ዘረጋ

Date:

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) በከተማዋ ከ482 ሺህ በላይ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎች አባል ለማድረግና አገልግሎቱን በቀላሉ እንዲያገኙ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች መዋቅሩን መዘርጋቱን አስታውቋል።

በዚህ አዲስ አደረጃጀት መሰረት በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ አንድ ሰብሳቢን ጨምሮ ዘጠኝ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በአመራርነት ተመድበዋል። በተጨማሪም የምክር ቤቱን ተግባራት የሚያስተባብሩ ሰራተኞች በቅርቡ እንደሚመደቡ ተገልጿል።

ይህ አዲስ አደረጃጀት በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል፣ አላማውም አባላትን በስፋት ማሳተፍና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ ነው ተብሏል።

KGEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...