የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሰኞ ዕለት ከዩክሬን፣ ከእንግሊዝ እና ከጀርመን መሪዎች ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ፣ ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከጀርመኑ ቻንስለር ጋር በሚያደርጉት በዚህ ስብሰባ፣ በዩክሬን ዙሪያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና እየተካሄዱ ያሉ ድርድሮችን ‘ለመገምገም’ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ስብሰባው የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነትና ሰላም አማራጮች ዙሪያ የጋራ አቋም ለመያዝ እና ለኪየቭ የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር ጠቃሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
