ሠራተኞች ይመዘናሉ እንጂ ከሥራ አይቀነሱም

Date:

ሠራተኛውን በመመዘን የማብቃት ሥራ ይከናወናል እንጂ የመንግሥት ሠራተኞች ከሥራ አይቀነሱም ሲል የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ወቅታዊ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ባሉ የሪፎርም ሥራዎች ላይዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሠራተኞች በቂ ዕውቀት አግኝተው በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ ኮሚሽኑ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ተመዝነው ስልጠና በመውሰድ ለሥራቸው ብቁ እንዲሆኑ እንደሚደረግም አንስተዋል።

ብቃት ያላቸውና የሌላቸው ሠራተኛ በምዘና ተለይተው ብቃት ላላቸውም ሆነ ለሌላቸው ተገቢው ስልጠና እንዲሰጥ ይደረጋል እንጂ ሠራተኛ መቀነስ የሚባል ነገር የለም ብለዋል።

ኮሚሽኑ እየሠራቸው ያሉ የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በማስቻል ረገድ የመንግሥት ሠራተኛው ዋነኛ ተዋናይ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር መኩሪያ፤ ሠራተኛው በተሰማራበት የሥራ መስክ ውጤታማ መሆን እንደሚገባው አመላክተዋል።

በተጨማሪም ለሪፎርሙ ውጤታማነት ተገልጋዩ ኃላፊነት አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ጥሩ የሚሠሩ ሠራተኞችን ማመስገን እና እጅ መንሻ የሚጠይቁትን መገሰፅ ይገባል ብለዋል።

የተጀመረው ለውጥ እንዲሳካ የመሪ ሚና ይዞ ሥራን ማከናወን እንደሚገባ አንስተው፤ አመራሮች ሥራን ለሠራተኛ ቆጥሮ መስጠትና ቆጥሮ መቀበል መቻል አለባቸውም ሲሉ ተናግረዋል።

ከሠራተኞች ደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያም የመንግሥት ሠራተኞች በሚመሩበት አዋጅ መሠረት በየአራት ዓመቱ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲሁም የሥራ አፈጻጸም በአግባቡ ለተሞላለት ሠራተኛ በየሁለት ዓመቱ የእርከን ጭማሪ እንደሚደረግ መደንገጉን አንስተዋል።

ይህ በአግባቡ ከተተገበረ የተከማቹ ችግሮችን መፍታት እንደሚቻልም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ችግር መፍታት የሚቻልበት አማራጭ ላይ በመንግሥት ደረጃ ሰፊ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ጠቅሰው፤ የክልል መግሥታትም ትኩረት ሰጥተውት ቦታ በማዘጋጀትና ብድር በማመቻቸት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

(GNN)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...