ሳፋሪኮም በከፍተኛ ኪሳራ እና ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር እየተፈተነ መሆኑን ተገለፀ

Date:

የዓለም ባንክ እና የዲጂታል ልማት አጋርነት በቅርቡ ባወጡት “የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ግምገማ” ሪፖርት መሠረት፣ አዲስ የገባው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የገበያ ፈተናዎችን እየገጠመው ነው።

ሪፖርቱ ሳፋሪኮም በ2024 በጀት ዓመት 325 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጿል፤ አመታዊ ገቢው (53.6 ሚሊዮን ዶላር) ለፈቃድ ክፍያው ወጪ እንኳን በቂ አይደለም ይላል።

ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ በመንግሥት ከተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ጋር እኩል ያልሆነ የመወዳደሪያ ሜዳ አለመፈጠሩ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም የፈቃድ ክፍያ አለመክፈሉ እና ሳፋሪኮም ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚደረጉ ጥሪዎች አማካኝነት በወር 1.6 ሚሊዮን ዶላር እንዲያጣ የሚያደርግ የጥሪ ዋጋ (MTR) ቅናሽ ማድረጉ የውድድሩን ፍትሐዊነት ጎድቶታል።

በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም የሳፋሪኮም መተግበሪያዎችን አግዷል እና በቴሌብር የዳታ ግዢ ላይ ቅናሽ በማድረግ ደንበኞችን በኔትወርኩ ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ተብሏል።

ዓለም ባንክ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን (ECA) እንደ ስታርሊንክ ላሉ የሳተላይት ኦፕሬተሮች ፈቃድ እንዲሰጥ፣ የፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱን እንዲያስተካክል እና በፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር ዙሪያ የተነሱትን ስጋቶች በጥልቀት እንዲመረምር መክሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...