ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቴሌኮም ገበያው ሦስተኛ ተወዳዳሪ  ቢገባም ስጋት የለብኝም አለ

Date:

“በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ሽፋን ኢትዮጵያ በጥቂት
ዓመታት ኬንያና ታንዛኒያ ከደረሱበት ደረጃ ላይ ትደርሳለች”

ሳፋሪኮም ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ሦስተኛ ተወዳዳሪ ኩባንያ ቢገባም፣ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ እድገት ላይ ስጋት እንደማይፈጥር ገልጧል።

የሳፋሪኮም ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፒተር ንዴግዋ ከዓለማቀፉ የዲጂታል የዜና ምንጭ ሞባይል ወርልድ ላይቭ ድረገጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ሦስተኛ ተወዳዳሪ ኩባንያ በሚገባበት ወቅት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተደላደለ መሠረት ላይ እንደሚደርስ እምነታቸውን ገልጸዋል።

ኩባንያው ወደ አገሪቱ ሲገባ የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት ሽፋን ዝቅተኛ እንደነበር የገለጡት ሥራ አስፈጻሚው፣ ውድድሩ ደንበኞች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል ብለዋል።

ሥራ አስፈጻሚው፣ ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ በሦስት ዓመታት ያፈራቸውን 10 ሚሊዮን ደንበኞች ኬንያ ውስጥ ለማፍራት 8 ዓመታት ፈጅቶበት እንደነበርም ጠቅሰዋል።

በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ሽፋን ኢትዮጵያ በጥቂት ዓመታት ኬንያና ታንዛኒያ ከደረሱበት ደረጃ ላይ እንደምትደርስም ሥራ አስፈጻሚው መጠቆማቸውን ዋዜማ ዘግባለች፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...