“ስምምነት ላይ አልተደረሰም ግን ተስፋ ሰጪ ነው” ፑቲንና ትራምፕ

Date:

አለም በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የፑቲንና የትራምፕ ውይይት ያለ ስምምነት ቢጠናቀቅም  ተስፋ ሰጪ እንደነበር መሪዎቹ ገልጸዋል ።

ትራምፕ ከፑቲን ጋር የካሄዱትን የመሪዎች ስብሰባ ከ0 እስከ 10 ባለው ሚዛን “አስር” እንደሚሰጡት ተናግረዋል
ትራምፕ ከፑቲን ጋር ባደረጉት ውይይት ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል ብለዋል።

ዩክሬንን በተመለከተ ብዙ ነጥቦች ላይ እንደተስማሙና በቀሪዎቹ ጉዳዮች ዙሪያ ለመስማማት ጥሩ እድሎች መፈጠራቸውን ተናግረዋል።

ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ ከፑቲን ጋር የተደረሰውን መግባቢያ የመጨረሻ ስምምነት እንዳልሆነና መጀመሪያ የሁሉም ወገኖች ስምምነት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ፑቲን እና ትራምፕ  ለ10 ደቂቃ ያህል መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በግል  በነበራቸው ቆይታ  ላይ ለውጦች መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቶቹ ለውጦች ተመዝግበዋል ቢሉም “የዩክሬኑን ጦርነት መቋጨት” በሚለው ጉዳይ ላይ ግን ያለ ምንም መስማማት ተለያይተዋል።

ፑቲን አስፈሪውን ጦርነት የመቋጨት ፍላጎቱ እንዳላቸው ቢያሳውቁም ለጦርነቱ መንስዔ የሆኑ ጉዳዮች ሁሉ ከስር መሰረቱ መላ ሊበጅላቸው ይገባል የሚል አቋም አላቸው።

ዩክሬን እና አውሮፓውያን በንግግሮች ላይ አሻጥርራቸውን ማቆም እንዳለባቸውም ቭማድሚር ፑቲን አሳስበዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ቀጣይ ወደ ሞስኮ ሊያቀኑ እንደሚችሉም ፑቲን ሀሳብ ሰተዋል።

ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓታት ይወያያሉ የተባሉት ፑቲንና ትራምፕ ሶስት ሰዓታት እንኳን ሳያወሩ ስብሰባቸውን አጠናቀዋል።

ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ጋር በአላስካ ካደረጉት ውይይት በኋላ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት አስተያየት፤ በብዙ ነጥቦች ላይ ተስማምተናል ብለዋል።

ትራምፕ ከፑቲን ጋር የነበራቸው ግኑኝነት በጣም ጥሩ በመሆኑ ለተጨማሪ 2-3 ሳምንታት ስለ አዲስ የሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ እንደማያስቡ ገልፀዋል።

ትራምፕ “ስምምነት ፍጠር ይገባል። ሩሲያ በጣም ትልቅ ኃይል ነች” ብለዋል ሲል  ስፑትኒክ ዘግቧል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...